በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው?

የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ለማድረግ ቁልፉ ምንድን ነው?
  • ፍቅር ነው?

  • ገንዘብ ነው?

  • ወይስ ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ደስተኞችስ የአምላክን ቃል ሰምተው የሚጠብቁት ናቸው!”—ሉቃስ 11:28 አዲስ ዓለም ትርጉም

ይህን ማወቅህ ለአንተ ምን ጥቅም አለው?

በቤተሰብህ ውስጥ እውነተኛ ፍቅር ይኖራል።—ኤፌሶን 5:28, 29

እርስ በርሳችሁ ከልብ ትከባበራላችሁ።—ኤፌሶን 5:33

የጠበቀ አንድነት ይኖራችኋል።—ማርቆስ 10:6-9

መጽሐፍ ቅዱስ በሚናገረው ነገር ላይ እምነት መጣል እንችላለን?

አዎ፣ ቢያንስ ሁለት ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል፦

  • የቤተሰብ መሥራች አምላክ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “እያንዳንዱ ቤተሰብ ስያሜውን ያገኘው” ከይሖዋ አምላክ እንደሆነ ይናገራል። (ኤፌሶን 3:14, 15) በሌላ አባባል የቤተሰብ ተቋም ሊኖር የቻለው ይሖዋ ስላዘጋጀው ነው። ይህን ማወቅ ምን ለውጥ ያመጣል?

    እስቲ አስበው፦ ጣፋጭ የሆነ ምግብ እየተመገብክ ቢሆንና ከምን እንደተዘጋጀ ለማወቅ ብትፈልግ ማንን ትጠይቃለህ? ምግቡን ያዘጋጀውን ሰው እንደምትጠይቅ የታወቀ ነው።

    በተመሳሳይም የቤተሰብን ሕይወት ደስተኛ ለማድረግ የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማወቅ የምንችለው የቤተሰብ መሥራች ከሆነው ከይሖዋ ነው።—ዘፍጥረት 2:18-24

  • አምላክ ስለ አንተ ያስባል። ቤተሰቦች ይሖዋ በቃሉ አማካኝነት የሚሰጣቸውን ምክር መስማታቸው ይጠቅማቸዋል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “እሱ ስለ እናንተ ያስባል” ይላል። (1 ጴጥሮስ 5:6, 7) ይሖዋ ለአንተ ከሁሉ የተሻለው ምን እንደሆነ ያውቃል፤ ምክሩም ምንጊዜም መሬት ጠብ የማይል ነው!—ምሳሌ 3:5, 6፤ ኢሳይያስ 48:17, 18

ምን ይመስልሃል?

ጥሩ ባል፣ ጥሩ ሚስት ወይም ጥሩ ወላጅ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠው መልስ ኤፌሶን 5:1, 2 እና ቆላስይስ 3:18-21 ላይ ይገኛል።