በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 19

የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው?

የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው?

እኛ የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደሆንን እናምናለን። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? የምናምንበት ነገር በምን ላይ የተመሠረተ እንደሆነ፣ የይሖዋ ምሥክሮች ተብለን የምንጠራው ለምን እንደሆነና በመካከላችን ምን ያህል ጠንካራ ፍቅር እንዳለ ማወቅህ እንዲህ የምንልበትን ምክንያት ለመረዳት ያስችልሃል።

1. የይሖዋ ምሥክሮች የሚያምኑበት ነገር በምን ላይ የተመሠረተ ነው?

ኢየሱስ “[የአምላክ ቃል] እውነት ነው” ብሏል። (ዮሐንስ 17:17) ልክ እንደ ኢየሱስ ሁሉ የይሖዋ ምሥክሮችም የሚያምኑበት ነገር ምንጊዜም በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ ነው። እስቲ የይሖዋ ምሥክሮች ያሳለፉትን ታሪክ ተመልከት። የይሖዋ ምሥክሮች ቀደም ሲል የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ተብለው ይጠሩ ነበር። በ19ኛው መቶ ዘመን መጨረሻ አካባቢ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቹ የአምላክን ቃል በጥንቃቄ መመርመር የጀመሩ ሲሆን የሚያምኑበት ነገር ሙሉ በሙሉ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን አድርገዋል። አብያተ ክርስቲያናት ከሚያስተምሩት ትምህርት የተለየ አቋም መያዝ በሚኖርባቸው ጊዜም እንኳ እንዲህ ከማድረግ ወደኋላ አላሉም። በኋላም እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነቶች ለሌሎች መናገር ጀመሩ። a

2. የይሖዋ ምሥክሮች ተብለን የምንጠራው ለምንድን ነው?

ይሖዋ አገልጋዮቹን ‘ምሥክሮቼ’ በማለት ይጠራቸዋል፤ ምክንያቱም ስለ እሱ እውነቱን ይናገራሉ። (ዕብራውያን 11:4–12:1) በጥንት ዘመን አምላክ ሕዝቡን “እናንተ ምሥክሮቼ ናችሁ” ብሏቸዋል። (ኢሳይያስ 43:10⁠ን አንብብ።) ኢየሱስ “ታማኝ ምሥክር” ተብሎ ተጠርቷል። (ራእይ 1:5) በመሆኑም በ1931 እኛም “የይሖዋ ምሥክሮች” ተብለን መጠራት ጀመርን። በዚህ ስም በመጠራታችን ኩራት ይሰማናል።

3. የይሖዋ ምሥክሮች ልክ እንደ ኢየሱስ ፍቅር የሚያሳዩት እንዴት ነው?

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ጥልቅ ፍቅር ነበረው፤ እንዲያውም ደቀ መዛሙርቱን እንደ ቤተሰቡ አድርጎ ይቆጥራቸው ነበር። (ማርቆስ 3:35⁠ን አንብብ።) የይሖዋ ምሥክሮችም አንድነት ያለው ዓለም አቀፍ ቤተሰብ ናቸው። አንዳችን ሌላውን ወንድም እና እህት እያልን የምንጠራው ለዚህ ነው። (ፊልሞና 1, 2) በተጨማሪም “ለመላው የወንድማማች ማኅበር ፍቅር ይኑራችሁ” የሚለውን ትእዛዝ እንፈጽማለን። (1 ጴጥሮስ 2:17) የይሖዋ ምሥክሮች እርስ በርስ እንደሚዋደዱ በብዙ መንገዶች ያሳያሉ፤ ለምሳሌ በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻቸውን በችግር ጊዜ ይረዳሉ።

ጠለቅ ያለ ጥናት

የይሖዋ ምሥክሮችን ታሪክ በስፋት እንመለከታለን፤ እንዲሁም የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደሆኑ የሚያሳዩ ተጨማሪ ማስረጃዎችን እንመረምራለን።

እውነተኛ ክርስቲያኖች የሚያምኑበት ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው፤ በተጨማሪም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለሌሎች ይናገራሉ

4. የምናምንበት ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ ነው

ይሖዋ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ግልጽ እየሆነ እንደሚሄድ አስቀድሞ ተናግሯል። ዳንኤል 12:4ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የአምላክ ሕዝቦች መጽሐፍ ቅዱስን መመርመራቸውን ሲቀጥሉ ምን “ይበዛል”?

ቻርልስ ራስልን ጨምሮ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የአምላክን ቃል ያጠኑ የነበረው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • በቪዲዮው ላይ እንደታየው ቻርልስ ራስልና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የአምላክን ቃል ያጠኑ የነበረው እንዴት ነው?

ይህን ታውቅ ነበር?

በምናምንባቸው ነገሮች ላይ ማስተካከያ ያደረግንባቸው ጊዜያት አሉ። ለምን? የፀሐይ ብርሃን እየደመቀ ሲሄድ በአንድ አካባቢ ያሉትን ነገሮች በደንብ ማየት እንደሚቻል ሁሉ አምላክም በቃሉ ውስጥ የሚገኘው እውነት ቀስ በቀስ ግልጽ እየሆነልን እንዲሄድ አድርጓል። (ምሳሌ 4:18⁠ን አንብብ።) ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ባይለወጥም ግንዛቤያችን እየተሻሻለ ሲሄድ እናምንበት በነበረው ነገር ላይ ማስተካከያ እናደርጋለን።

5. ከምንጠራበት ስም ጋር በሚስማማ መንገድ እንኖራለን

የይሖዋ ምሥክሮች ተብለን የምንጠራው ለምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የይሖዋ ምሥክሮች የሚለው መጠሪያ እኛን በደንብ አድርጎ ይገልጸናል የምንለው ለምንድን ነው?

ይሖዋ ሰዎችን ምሥክሮቹ አድርጎ የመረጠው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ስለ እውነተኛው አምላክ ብዙ ውሸቶች ተነግረዋል፤ በመሆኑም ምሥክሮቹ ስለ እሱ እውነቱ እንዲታወቅ ያደርጋሉ። ስለ አምላክ ከሚነገሩ ውሸቶች መካከል ሁለቱን እንመልከት።

አንዳንድ ሃይማኖቶች አምላክ ምስሎችን ተጠቅመን እንድናመልከው እንደሚፈልግ ለተከታዮቻቸው ያስተምራሉ። ሆኖም ይህ እውነት ነው? ዘሌዋውያን 26:1ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በዚህ ጥቅስ መሠረት እውነታው ምንድን ነው? ይሖዋ ምስሎችን ለአምልኮ ስለመጠቀም ምን ይሰማዋል?

አንዳንድ የሃይማኖት መሪዎች ኢየሱስ ሁሉን ቻይ አምላክ እንደሆነ ያስተምራሉ። ሆኖም ይህ እውነት ነው? ዮሐንስ 20:17ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • በዚህ ጥቅስ መሠረት እውነታው ምንድን ነው? ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክና ኢየሱስ አንድ ናቸው?

  • ይሖዋ ስለ እሱና ስለ ልጁ እውነቱን እንዲናገሩ ምሥክሮቹን እንደላከ ማወቅህ ምን ስሜት ይፈጥርብሃል?

6. እርስ በርስ እንዋደዳለን

መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖችን ከተለያዩ የአካል ክፍሎች ጋር ያመሳስላቸዋል። አንደኛ ቆሮንቶስ 12:25, 26ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • እውነተኛ ክርስቲያኖች ሌሎች ክርስቲያኖች ሲሠቃዩ ሲያዩ ምን ይሰማቸዋል?

  • በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ስላለው ፍቅር ምን ያስተዋልከው ነገር አለ?

በአንድ አካባቢ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ችግር ሲደርስባቸው በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ፈጣን ምላሽ ይሰጣሉ። አንድ ምሳሌ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • የይሖዋ ምሥክሮች በአደጋ ጊዜ የሚያደርጉት እርዳታ እርስ በርሳቸው እንደሚዋደዱ የሚያሳየው እንዴት ነው?

እውነተኛ ክርስቲያኖች ችግር ለደረሰባቸው ሰዎች ፍቅር ያሳያሉ

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “የይሖዋ ምሥክሮች መጤዎች ናቸው።”

  • ይሖዋ አገልጋዮቹን ምሥክሮቼ ብሎ መጥራት የጀመረው መቼ ነው?

ማጠቃለያ

የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው። ስለ ይሖዋ እውነቱን የምናሳውቅ ዓለም አቀፍ ቤተሰብ ነን፤ የምናምንበት ነገር የተመሠረተው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው።

ክለሳ

  • የይሖዋ ምሥክሮች ተብለን የምንጠራው ለምንድን ነው?

  • እርስ በርስ እንደምንዋደድ የምናሳየው እንዴት ነው?

  • የይሖዋ ምሥክሮች እውነተኛ ክርስቲያኖች ናቸው ብለህ ታምናለህ?

ግብ

ምርምር አድርግ

የይሖዋ ምሥክሮች የሐሰት ትምህርቶችን ያጋለጡት እንዴት ነው?

የአምላክ ሕዝቦች ስሙን ያስከብራሉ (7:08)

የይሖዋ ምሥክሮችን በተመለከተ ለሚነሱብህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ትፈልጋለህ?

“ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች” (ድረ ገጻችን ላይ ያለ ዓምድ)

ስቲቨን፣ በነበረው የዘር ጥላቻ ተነሳስቶ የጭካኔ ድርጊት ይፈጽም ነበር። በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ያየው ነገር ለውጥ እንዲያደርግ ያነሳሳው እንዴት ነው?

“ሕይወቴ ከድጡ ወደ ማጡ ሄዶ ነበር” (መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1, 2015)

a መጠበቂያ ግንብ ተብሎ የሚጠራው ዋነኛው መጽሔታችን ከ1879 አንስቶ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ያለማቋረጥ ሲያቀርብ ቆይቷል።