ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት አጫውት ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት ርኅራኄ ኢየሱስ ፍጹም በመሆኑ፣ ሌሎች ሰዎች የሚያስጨንቋቸው ወይም የሚያሳስቧቸው ብዙዎቹ ነገሮች አልደረሱበትም። ያም ቢሆን ለሰዎች በጥልቅ እንደሚያዝን አሳይቷል። ሌሎችን ለመርዳት ሲል የራሱን ጥቅም መሥዋዕት ለማድረግ ይኸውም ከሚጠበቅበት አልፎ ለመሄድ ፈቃደኛ ነበር። በእርግጥም ሌሎችን ለመርዳት ያነሳሳው ርኅራኄ ነው። በሚከተሉት ምዕራፎች ላይ ያሉትን ምሳሌዎች ተመልከት፦ 32, 37, 57, 99 በቀላሉ የሚቀረብ ልጅ አዋቂ ሳይል በማንኛውም ዕድሜ ያሉ ሰዎች ኢየሱስን ይቀርቡት ነበር፤ ምክንያቱም ሰዎች፣ በሥራ የተወጠረና ትልቅ ቦታ ያለው እንደሆነ እንዲሰማቸው አላደረገም። ኢየሱስ ለሰዎች በግለሰብ ደረጃ ትኩረት ስለሚሰጥ ከእሱ ጋር መሆን አልከበዳቸውም። ይህን ለማስተዋል የሚከተሉትን ምዕራፎች ተመልከት፦ 25, 27, 95 የጸሎት ሰው ኢየሱስ ብቻውንም ሆነ ከሌሎች የይሖዋ አገልጋዮች ጋር ሆኖ ለአባቱ ልባዊ ጸሎት የማቅረብ ልማድ ነበረው። ምግብ ሲቀርብ ብቻ ሳይሆን በቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ ይጸልይ ነበር። አባቱን ለማመስገን፣ ለማወደስ እንዲሁም ከባድ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት የእሱን አመራር ለማግኘት ጸልዮአል። ምሳሌዎች ለማግኘት የሚከተሉትን ምዕራፎች ተመልከት፦ 24, 34, 91, 122, 123 ራስ ወዳድ አለመሆን ኢየሱስ እረፍት ወይም ዘና ማለት ቢያስፈልገውም እንኳ ለሌሎች ሲል የራሱን ጥቅም መሥዋዕት ያደረገባቸው ጊዜያት አሉ። እሱ ብቻ ቅድሚያ እንዲሰጠው የሚፈልግ ሰው አልነበረም። በዚህ ረገድም ቢሆን ልንከተለው የምንችል አርዓያ ትቶልናል። ኢየሱስ የተወውን አርዓያ በሚከተሉት ምዕራፎች ላይ አንብብ፦ 19, 41, 52 ይቅር ባይነት ኢየሱስ፣ ይቅር ባይ መሆን አስፈላጊ እንደሆነ በማስተማር ብቻ አልተወሰነም፤ ከደቀ መዛሙርቱም ሆነ ከሌሎች ጋር ባለው ግንኙነት ይቅር ባይ ነበር። የሚከተሉት ምዕራፎች በያዟቸው ምሳሌዎች ላይ አሰላስል፦ 26, 40, 64, 85, 131 ቅንዓት አብዛኞቹ አይሁዳውያን መሲሑን እንደማይቀበሉትና ጠላቶቹ እንደሚገድሉት በትንቢት ተነግሮ ነበር። በመሆኑም ኢየሱስ ሰዎችን ለመርዳት ያን ያህል ጥረት ባያደርግ የሚያስገርም አይሆንም ነበር። እሱ ግን እውነተኛውን አምልኮ በቅንዓት አራምዷል። ሰዎች፣ ቸልተኛ ይባስ ብሎም ተቃዋሚ በሆኑባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ተከታዮቹ ሁሉ በዚህ ረገድ ግሩም ምሳሌ ትቷል። የሚከተሉትን ምዕራፎች ተመልከት፦ 16, 72, 103 ትሕትና ኢየሱስ እውቀትንና ጥበብን ጨምሮ ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች፣ ፍጹም ካልሆኑ የሰው ልጆች ይበልጣል። ፍጹም መሆኑ አብረውት ከነበሩት ሰዎች ሁሉ በአካላዊ ሁኔታም ሆነ በአስተሳሰቡ የላቀ እንዲሆን እንዳደረገው ምንም ጥርጥር የለውም። ያም ቢሆን በትሕትና ሌሎችን አገልግሏል። በሚከተሉት ምዕራፎች ላይ ምሳሌዎች ማግኘት ትችላለህ፦ 10, 62, 66, 94, 116 ትዕግሥት ሐዋርያቱም ሆነ ሌሎች ሰዎች የእሱን አርዓያ ሳይከተሉ ወይም የተናገረውን በተግባር ሳያውሉ በሚቀሩበት ጊዜ ሁሉ በትዕግሥት ይይዛቸው ነበር። እነዚህ ሰዎች ወደ ይሖዋ ይበልጥ መቅረብ እንዲችሉ ሲል የሚያስፈልጓቸውን ትምህርቶች ደጋግሞ ይነግራቸው ነበር። ኢየሱስ ትዕግሥት ያሳየባቸውን ምሳሌዎች ለማግኘት የሚከተሉትን ምዕራፎች ተመልከት፦ 74, 98, 118, 135 ተመለስ ቀጥል ተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች ኢየሱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው እነዚህንስ አይተሃቸዋል? የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ትምህርቶች ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው? ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው? ወይስ ሁሉን ቻይ ከሆነው አምላክ የተለየ አካል ነው? መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ኢየሱስ የሞተው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ሞት ለሰው ልጆች ከፍተኛ ጥቅም እንዳስገኘ ይናገራል። ለመሆኑ የኢየሱስ ሞት ምን ጥቅም አስገኝቷል? መጠበቂያ ግንብ ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ኢየሱስ ጥሩ ነገር ሠርቶ ያለፈ ሰው ብቻ ነበር? የናዝሬቱ ኢየሱስ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የበለጠ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር የቻለው ለምንድን ነው? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ኢየሱስ ምን ይመስል ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ምን ይመስል እንደነበር የሚጠቁም የተወሰነ ፍንጭ ይሰጠናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ለምን አትሞክረውም? አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ከአስተማሪ ጋር። አትም አጋራ አጋራ ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት አማርኛ ኢየሱስን ለመምሰል የሚያስችሉ ባሕርያት https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1102014752/univ/art/1102014752_univ_sqr_xl.jpg jy ገጽ 317