ትምህርት 7
የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
1. የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
የአምላክ መንግሥት በሰማይ የሚገኝ መስተዳድር ነው። ይህ መንግሥት ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ አጥፍቶ የአምላክ ፈቃድ በሰማይም ሆነ በምድር ላይ እንዲፈጸም ያደርጋል። ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸው መልእክት የምሥራች ነው። በቅርቡ የአምላክ መንግሥት፣ ጥሩ አገዛዝ ለማግኘት ያለንን ፍላጎት ያሟላልናል። በምድር ላይ የሚኖሩ በሙሉ አንድነት እንዲኖራቸው ያደርጋል።—ዳንኤል 2:44ን፣ ማቴዎስ 6:9, 10ን እና 24:14ን አንብብ።
የትኛውም መንግሥት፣ ንጉሥ ሊኖረው እንደሚገባ የታወቀ ነው። ይሖዋ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን የመንግሥቱ ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል።—ራእይ 11:15ን አንብብ።
የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት
2. ኢየሱስ ብቃት ያለው ንጉሥ ነው የምንለው ለምንድን ነው?
የአምላክ ልጅ ደግና ትክክል የሆነውን ነገር ከማድረግ ወደኋላ የማይል በመሆኑ ብቃት ያለው ንጉሥ ነው። (ማቴዎስ 11:28-30) እንዲሁም ከሰማይ ሆኖ መላዋን ምድር ስለሚገዛ ሰዎችን ለመርዳት የሚያስችል አቅም አለው። ኢየሱስ ከሞት ከተነሳ በኋላ ወደ ሰማይ በመሄድ በይሖዋ ቀኝ ሆኖ ሥልጣኑን እስኪያገኝ ድረስ ይጠባበቅ ጀመር። (ዕብራውያን 10:12, 13) በመጨረሻም መግዛት እንዲጀምር አምላክ ሥልጣን ሰጠው።—ዳንኤል 7:13, 14ን አንብብ።
3. ከኢየሱስ ጋር አብረው የሚገዙት እነማን ናቸው?
“ቅዱሳን” ተብለው የተጠሩ ሰዎችን ያቀፈ አንድ ቡድን ከኢየሱስ ጋር በመሆን በሰማይ ይገዛል። (ዳንኤል 7:27) ቅዱሳን እንዲሆኑ በመጀመሪያ የተመረጡት የኢየሱስ ታማኝ ሐዋርያት ነበሩ። ይሖዋ ቅዱሳን የሚሆኑ ታማኝ ወንዶችንና ሴቶችን አሁንም መምረጡን ቀጥሏል። እነዚህ ሰዎች ልክ እንደ ኢየሱስ ከሞት ሲነሱ መንፈሳዊ አካል ይኖራቸዋል።—ዮሐንስ 14:1-3ን እና 1 ቆሮንቶስ 15:42-44ን አንብብ።
ሉቃስ 12:32) አጠቃላይ ቁጥራቸው 144,000 ሲሆን ከኢየሱስ ጋር በመሆን ምድርን ይገዛሉ።—ራእይ 14:1ን አንብብ።
ወደ ሰማይ የሚሄዱት ሰዎች ምን ያህል ናቸው? ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች “ትንሽ መንጋ” በማለት ጠርቷቸዋል። (4. ኢየሱስ መግዛት ሲጀምር ምን ነገሮች ተከናወኑ?
የአምላክ መንግሥት መግዛት የጀመረው በ1914 ነው። * ኢየሱስ ንጉሥ እንደሆነ የወሰደው የመጀመሪያ እርምጃ ሰይጣንንና አጋንንቱን ወደ ምድር መወርወር ነበር። ሰይጣን በዚህ በጣም ስለተቆጣ መላዋን ምድር ማመስ ጀመረ። (ራእይ 12:7-10, 12) ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሰው ልጆች ወዮታ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ሄዷል። ጦርነት፣ ረሃብ፣ ወረርሽኝና የምድር ነውጥ የአምላክ መንግሥት በቅርቡ ምድርን ሙሉ በሙሉ እንደሚቆጣጠር የሚጠቁመው “ምልክት” ክፍል ናቸው።—ሉቃስ 21:7, 10, 11, 31ን አንብብ።
5. የአምላክ መንግሥት ምን ያከናውናል?
የአምላክ መንግሥት በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የስብከት ሥራ አማካኝነት ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ እጅግ ብዙ ሕዝብ አንድነት እንዲኖራቸው እያደረገ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች በኢየሱስ የሚመራው የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች እየሆኑ ነው። ይህ መንግሥት በምድር ላይ ያለውን ክፉ ሥርዓት በሚያጠፋበት ጊዜ እነዚህን ሰዎች ያድናቸዋል። እንግዲያው ከአምላክ መንግሥት ጥቅም ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለኢየሱስ መታዘዝን መማር ይኖርባቸዋል።—ራእይ 7:9, 14, 16, 17ን አንብብ።
ይህ መንግሥት አምላክ ለሰው ዘር የነበረው የመጀመሪያ ዓላማ በ1,000 ዓመት ውስጥ እንዲፈጸም ያደርጋል። መላዋ ምድር ገነት ትሆናለች። በመጨረሻም ኢየሱስ መንግሥቱን ለአባቱ ያስረክባል። (1 ቆሮንቶስ 15:24-26) አንተስ ስለ አምላክ መንግሥት ልትነግረው የምትፈልገው ሰው አለ?—መዝሙር 37:10, 11, 29ን አንብብ።
^ አን.6 የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መንግሥቱ በ1914 መግዛት መጀመሩን የሚጠቁሙት እንዴት እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? የተባለውን መጽሐፍ ከገጽ 217-219 ተመልከት።