ትዳር ለመመሥረት በእርግጥ ዝግጁ ነን?
ምዕራፍ 30
ትዳር ለመመሥረት በእርግጥ ዝግጁ ነን?
ለትዳር የምትሆንህ ሴት አግኝተሃል፤ መጠናናት ከጀመራችሁ ስለቆያችሁ ከእሷ ጋር እውነተኛ ፍቅር እንደያዘህ እርግጠኛ ነህ። በቅርቡ ከእሷ ጋር አስደሳች የትዳር ሕይወት ስትመሩ ይታይሃል። ይሁንና ትልቅ ቦታ የሚሰጠውን ይህን ውሳኔ ለማድረግ በተቃረብክበት ወቅት የሚከተለው ጥያቄ ተፈጠረብህ . . .
ትዳር ለመመሥረት በእርግጥ ዝግጁ ነን?
ለትዳር የሚሆናችሁንና ከልብ የምትወዱትን ሰው ብታገኙም ለማግባት ስታስቡ ውሳኔያችሁ ትክክል መሆኑን መጠራጠር ትጀምሩ ይሆናል፤ ይህ የሚያስገርም አይደለም። ደስታ የራቃቸው ትዳሮች ከመብዛታቸውና
ፍቺ ከመስፋፋቱ አንጻር በሕይወታችሁ ላይ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣውን ይህን እርምጃ ከመውሰዳችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ማሰባችሁ ተገቢ ነው። ታዲያ ለትዳር ዝግጁ እንደሆናችሁ ማወቅ የምትችሉት እንዴት ነው? ስለ ትዳር ስታስቡ የሚመጡባችሁን የማይጨበጡ ተስፋዎች ከአእምሯችሁ በማውጣት ሚዛናዊ ሆናችሁ እውነታውን ማየት ያለባችሁ አሁን ነው። እስቲ አንዳንዶቹን እንመልከት፦የማይጨበጥ ተስፋ 1 “ፍቅር ካለ ሁሉ ነገር አለ።”
እውነታው፦ ፍቅር ብቻውን ወጪዎቻችሁን መሸፈንና ከገንዘብ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሟችሁን ችግሮች መወጣት እንደምትችሉ ዋስትና አይሆንም። እንዲያውም በትዳር ውስጥ ለሚፈጠሩ ግጭቶችና ውሎ አድሮም ለፍቺ ዋነኛ መንስኤ ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ ገንዘብ እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ለገንዘብ ያላችሁ አመለካከት ሚዛናዊ ካልሆነ መንፈሳዊና ስሜታዊ ጉዳት ሊያጋጥማችሁ ይችላል፤ እንዲሁም ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት ሊሻክር ይችላል። (1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10) ከዚህ ምን ትምህርት ማግኘት ይቻላል? ‘ስለ ገንዘብ አጠቃቀም ማውራቱን ከተጋባን በኋላ እንደርስበታለን’ ብላችሁ አታስቡ!
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ከእናንተ መካከል፣ ግንብ ለመገንባት ፈልጎ . . . በመጀመሪያ ተቀምጦ ወጪውን የማያሰላ ማን ነው?”—ሉቃስ 14:28
እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦ ከገንዘብ ጋር ስለተያያዙ ነገሮች ከመጋባታችሁ በፊት ተወያዩ። (ምሳሌ 13:10) እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን ተነጋገሩባቸው፦ ከገቢያችን አንጻር ምን ዓይነት በጀት ሊኖረን ይገባል? በሁለታችን ስም የተከፈተ የጋራ የባንክ ሒሳብ ቢኖረን ይሻላል ወይስ የየራሳችን የባንክ ሒሳብ ቢኖረን? ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ነገሮችን መዝግቦ የመያዙንና ወጪዎችን በጊዜው የመክፈሉን ኃላፊነት በተሻለ ሁኔታ መወጣት የምንችለው ማንኛችን ነን? * አንዳችን ሌላውን ሳናማክር ምን ያህል ገንዘብ ማውጣት እንችላለን? እንደነዚህ ባሉት ጉዳዮች ላይ ተመካክራችሁ ስምምነት ላይ መድረስ ያለባችሁ አሁን ነው!—መክብብ 4:9, 10
የማይጨበጥ ተስፋ 2 “ዓይን ለዓይን ተያይተን የምንግባባ ዓይነት ሰዎች ስለሆንን የማንስማማበት ነገር ገጥሞን አያውቅም፤ ስለዚህ ትዳራችን እንደሚሰምር ጥያቄ የለውም!”
እውነታው፦ በመካከላችሁ ጨርሶ አለመግባባት ተፈጥሮ የማያውቅ ከሆነ ይህ የሆነው የሐሳብ ልዩነት ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን ላለማንሳት ስለምትጠነቀቁ ሮም 3:23፤ ያዕቆብ 3:2) ‘ምን ያህል እንጣጣማለን’ የሚለውን ብቻ ሳይሆን ‘አለመግባባት ሲፈጠር ምን እናደርጋለን’ የሚለውንም ጉዳይ ልታስቡበት ይገባል። በሁለት ሰዎች መካከል ያለው ግንኙነት ጠንካራ ነው የሚባለው በመካከላቸው የአመለካከት ልዩነት መኖሩን አምነው የሚቀበሉ እንዲሁም ልዩነታቸውን ብስለት በሚንጸባረቅበትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት የሚችሉ ከሆነ ነው።
ሊሆን ይችላል። ጋብቻ ውስጥ ከገባችሁ በኋላ ግን ከእነዚህ ጉዳዮች ማምለጥ አትችሉም። እንደ እውነቱ ከሆነ ፍጹማን ያልሆኑ ሁለት ሰዎች በሁሉም ነገር ተመሳሳይ አመለካከት ሊኖራቸው አይችልም፤ በመሆኑም የማይግባቡባቸው ጉዳዮች መኖራቸው አይቀርም። (መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ቁጣችሁን አውላችሁ [አታሳድሩ]።”—ኤፌሶን 4:26 ሕያው ቃል
እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦ ከወላጆቻችሁ እንዲሁም ከወንድሞቻችሁና ከእህቶቻችሁ ጋር አለመግባባት ሲፈጠር እንዴት ትፈቱት እንደነበር መለስ ብላችሁ አስቡ። በዚህ መጽሐፍ ገጽ 93 ወይም በጥራዝ 2 ገጽ 221 ላይ ከሚገኘው ጋር የሚመሳሰል ሠንጠረዥ ሥሩ። ከዚያም አለመግባባቱ እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑትን ሁኔታዎች፣ በወቅቱ የወሰዳችሁትን እርምጃ እና የተሻለ ይሆን ነበር ብላችሁ የምታስቡትን እርምጃ ጻፉ። ለምሳሌ በወቅቱ የወሰዳችሁት ስሜታዊ እርምጃ ተመናጭቃችሁ ወደ ክፍላችሁ በመሄድ በሩን ማላተም ከነበረ፣ የተሻለ ይሆን ነበር ብላችሁ የምታስቡትን እርምጃ ጻፉ፤ በሌላ አባባል ችግሩን የሚያባብሰውን ሳይሆን መፍትሔ ሊያመጣ የሚችለውን አማራጭ አስፍሩ። አለመግባባቶችን በተሻለ መንገድ እንዴት መፍታት እንደምትችሉ ከአሁኑ ከተማራችሁ ለደስተኛ ትዳር ወሳኝ ከሆኑት ልማዶች አንዱን ማዳበር ትችላላችሁ።
የማይጨበጥ ተስፋ 3 “ካገባሁ የፆታ ፍላጎቴን በማንኛውም ጊዜ ማርካት እችላለሁ።”
1 ቆሮንቶስ 10:24) እውነቱን ለመናገር፣ ራስን የመግዛት ባሕርይ ማዳበር ያለብህ ነጠላ እያለህ ብቻ ሳይሆን ካገባህ በኋላም ነው።—ገላትያ 5:22, 23
እውነታው፦ ትዳር ስለመሠረትህ ብቻ በፈለግኸው ጊዜ የፆታ ግንኙነት መፈጸም ትችላለህ ማለት አይደለም። የትዳር ጓደኛህ እንደ አንተው ሰው መሆኗንና ስሜቷ ሊከበርላት እንደሚገባ አትርሳ። ለምሳሌ የትዳር ጓደኛህ ጥሩ ስሜት ላይ ባለመሆኗ የፆታ ግንኙነት መፈጸም የማትፈልግበት ጊዜ ሊኖር ይችላል። ስላገባህ ብቻ የፈለግኸውን ነገር በፈለግኸው ጊዜ የማግኘት መብት እንዳለህ ሊሰማህ አይገባም። (መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? ‘ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ዕቃ እንዴት በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት ማወቅ አለበት፤ ይህም ለፍትወተ ሥጋ በመጎምጀት አይሁን።’—1 ተሰሎንቄ 4:4, 5
እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦ ከፆታ ስሜት ጋር በተያያዘ ስላለህ ዝንባሌ እና ልማድ ቆም ብለህ ልታስብበት ይገባል፤ ይህ ሁኔታ የትዳር ሕይወትህን የሚነካው እንዴት እንደሆነ አስብ። ለምሳሌ ያህል፣ ለራስህ ስሜት ብቻ እንድታስብ የሚያደርገው ማስተርቤሽን የመፈጸም ልማድ ወጥመድ ሆኖብሃል? የብልግና ምስሎችን ትመለከታለህ? ተቃራኒ ፆታን በመከጀል ሰረቅ አድርገህ የመመልከት ልማድ አለህ? ከሆነ ራስህን እንዲህ እያልክ ጠይቅ፦ ‘ከማግባቴ በፊት የፆታ ስሜቴን መቆጣጠር ካልቻልኩ ካገባሁ በኋላ ይህን ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?’ (ማቴዎስ 5:27, 28) ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ነገር ደግሞ የሚከተለው ነው፦ የማሽኮርመም ልማድ ስላለህ ወይም በአንድ የማትረጋ በመሆንህ ምክንያት መጥፎ ስም አትርፈሃል? ከሆነ ትዳር ከመሠረትህ በኋላ በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማትችልና የፍቅር ስሜት ማሳየት የሚኖርብህ ለትዳር ጓደኛህ ብቻ እንደሆነ አስበህበታል?—ምሳሌ 5:15-17
የማይጨበጥ ተስፋ 4 “ማግባት ደስተኛ ያደርገኛል።”
እውነታው፦ ከማግባቱ በፊት ደስተኛ ያልሆነ ሰው አብዛኛውን ጊዜ ካገባ በኋላም ደስተኛ አይሆንም። ለምን? ምክንያቱም አንድ ሰው ደስተኛ መሆን አለመሆኑ የተመካው ምሳሌ 15:15) አፍራሽ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ትዳር ቢመሠርቱም ትኩረት የሚያደርጉት ባገኟቸው ጥሩ ነገሮች ላይ ሳይሆን በጎደሏቸው ነገሮች ላይ ነው። ስለዚህ ነጠላ እያላችሁ አዎንታዊ አመለካከት ለማዳበር እና ይህን መንፈስ ይዛችሁ ለመቀጠል ጥረት ማድረጋችሁ የተሻለ ነው። እንዲህ ካደረጋችሁ ካገባችሁ በኋላም ስለ ትዳራችሁ አዎንታዊ አመለካከት ይኖራችኋል፤ ይህ ደግሞ የትዳር ጓደኛችሁም ተመሳሳይ መንፈስ እንዲኖረው ያደርጋል።
ባለበት ሁኔታ ላይ ሳይሆን በአመለካከቱ ላይ ነው። (መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ለምኞት ከመገዛት ይልቅ ባለ ነገር መርካት ይሻላል።”—መክብብ 6:9 የታረመው የ1980 ትርጉም
እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦ አንዳንድ ጊዜ አፍራሽ አመለካከት እንዲኖረን የሚያደርገው ከእውነታ የራቁ ነገሮችን መጠበቅ ነው። ከትዳር የምትጠብቋቸውን ሁለት ወይም ሦስት ነገሮች በወረቀት ላይ ጻፉ። ከዚያም የጻፋችሁትን መለስ ብላችሁ በመመልከት ራሳችሁን እንደሚከተለው ብላችሁ ጠይቁ፦ ‘ከትዳር ለማግኘት
የምጠብቀው ነገር ሊፈጸም የማይችል ከንቱ ምኞት ነው? በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፈው ነገር ምናልባትም በፍቅር ፊልሞች ወይም መጻሕፍት ላይ የሚንጸባረቁት ነገሮች ተጽዕኖ አድርገውብኝ ይሆን? የማስበው እኔ ከትዳር ስለማገኘው ጥቅም ብቻ ነው? ለምሳሌ ማግባት የምፈልገው የብቸኝነት ስሜቴን ለማስወገድ፣ የፆታ ስሜቴን ለማርካት ወይም የእኩዮቼን አክብሮት ለማግኘት ስል ነው?’ ከሆነ አንተ ስለምታገኘው ጥቅም ብቻ ሳይሆን ስለ ሁለታችሁም ማሰብ መጀመር ይኖርብሃል። አንተም ሆንክ ልታገባት የምታስባት ሴት ከትዳር ልታገኟቸው የምትችሏቸውን ሁለት ወይም ሦስት ነገሮች መጻፍህ አመለካከትህን ለማስተካከል ይረዳሃል።ከላይ እንደተገለጹት ያሉ የማይጨበጡ ተስፋዎች ትዳር ብትመሠርት ደስተኛ እንዳትሆን ሊያደርጉህ ይችላሉ። ስለዚህ እንዲህ ያለውን አመለካከት አስወግደህ እውነታውን ለማየት ጥረት አድርግ። አንተም ሆንክ የምታገባት ሴት በገጽ 216 እና 217 ላይ የሚገኘውን መልመጃ መሥራታችሁ በሕይወታችሁ ውስጥ ትልቅ በረከት እንድታገኙ ይኸውም ደስተኛ ትዳር መመሥረት እንድትችሉ ይረዳችኋል።—ዘዳግም 24:5፤ ምሳሌ 5:18
መለያየት የሞት ያህል ሊከብድ ይችላል። እንዲህ ዓይነቱን ሁኔታ መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?
[የግርጌ ማስታወሻ]
^ አን.9 በምሳሌ 31:10-28 ላይ የተጠቀሰችው ‘ጠባየ መልካም ሚስት’ ከገንዘብ ጋር በቀጥታ የተያያዙ በርካታ ከባድ ኃላፊነቶችን እንደምትወጣ ተገልጿል። ቁጥር 13, 14, 16, 18 እና 24ን ተመልከት።
ቁልፍ ጥቅስ
“ሰው ከአባቱና ከእናቱ ተለይቶ ከሚስቱ ጋር ይጣመራል፤ ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።”—ዘፍጥረት 2:24
ጠቃሚ ምክር
አዲስ ባለትዳሮች ስኬታማ ትዳር ለመመሥረት ምን እንደሚረዳቸው ለማወቅ በትዳር ውስጥ የቆዩ ባልና ሚስትን ምክር ጠይቅ።—ምሳሌ 27:17
ይህን ታውቅ ነበር?
ስኬታማ ትዳር ያላቸው ባልና ሚስት አንዳቸው ለሌላው ጓደኛ ናቸው፤ የልባቸውን አውጥተው ይነጋገራሉ፤ አለመግባባት ሲያጋጥማቸው እንዴት እንደሚፈቱት ያውቃሉ እንዲሁም ትዳራቸውን የዕድሜ ልክ ጥምረት እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል።
ላደርጋቸው ያሰብኳቸው ነገሮች
ወደፊት ትዳር ስመሠርት ከትዳር ጓደኛዬ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዲኖረን አሁን ላዳብረው የሚገባ ባሕርይ ․․․․․
ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ወላጆቼን ልጠይቃቸው የምፈልገው ነገር ․․․․․
ምን ይመስልሃል?
● በአንዳንድ አገሮች የፍቺ ቁጥር ከፍተኛ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያት ምን ይመስልሃል?
● ከቤተሰብህ አባላት ጋር ባለህ ግንኙነት ደስተኛ ስላልሆንህ ይህን ለመገላገል ብለህ ብቻ ትዳር መመሥረትህ ምን አደጋዎች አሉት?
● ወደፊት ትዳር ስትመሠርት የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያዎች በጥብቅ ለመከተል ጥረት ማድረግህ ጠቃሚ የሆነው ምንድን ነው?
[በገጽ 220 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
“ትዳር መመሥረት ትልቅ ውሳኔ ነው። ምን ዓይነት ኃላፊነት ውስጥ እየገባህ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ዓይነት ኃላፊነት ውስጥ የምትገባው ከማን ጋር እንደሆነም በሚገባ ማወቅ ይኖርብሃል።”—ኦድሬ
[በገጽ 216 እና 217 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
የመልመጃ ሣጥን
ትዳር ለመመሥረት ዝግጁ ነህ?
በእነዚህ ሁለት ገጾች ላይ ያሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው። እንዲያውም እነዚህን ጥያቄዎች ልታገባት ካሰብሃት ሴት ጋር ልትወያዩባቸው ትችላላችሁ። ጥቅሶቹን አውጥታችሁ መመልከታችሁ በጣም አስፈላጊ ነው።
ገንዘብ
□ ለገንዘብ ምን አመለካከት አለህ?—ዕብራውያን 13:5, 6
□ በገንዘብ አጠቃቀም ረገድ ኃላፊነት የሚሰማህ መሆንህን እያሳየህ ያለኸው እንዴት ነው?—ማቴዎስ 6:19-21
□ በአሁኑ ወቅት ዕዳ አለብህ? ከሆነ ዕዳህን ለመክፈል ምን እርምጃዎች እየወሰድህ ነው?—ምሳሌ 22:7
□ ለሠርጋችሁ ምን ያህል ለማውጣት አስባችኋል? የሠርግ ወጪያችሁን ለመሸፈን ገንዘብ መበደር ካሰባችሁ ምን ያህል መበደር ያለባችሁ ይመስላችኋል?—ሉቃስ 14:28
□ ከተጋባችሁ በኋላ ሁለታችሁም መሥራት ይኖርባችኋል? ከሆነ የሥራ ሰዓታችሁ የተለያየ ቢሆን ከመጓጓዣ ጋር በተያያዘ ምን እንደምታደርጉ አስባችሁበታል?—ምሳሌ 15:22
□ ከተጋባችሁ በኋላ የት ለመኖር አስባችኋል? ለቤት ኪራይ፣ ለምግብ፣ ለልብስ እና ለሌሎች ነገሮች ምን ያህል የምታወጡ ይመስላችኋል? እነዚህን ወጪዎቻችሁን የምትሸፍኑትስ እንዴት ነው?—ምሳሌ 24:27
ቤተሰብ
□ ከወላጆችህ እንዲሁም ከወንድሞችህና ከእህቶችህ ጋር መግባባት ይቸግርሃል?—ዘፀአት 20:12፤ ሮም 12:18
□ ከቤተሰብህ አባላት ጋር አለመግባባት ሲፈጠር የምትፈታው እንዴት ነው?—ቆላስይስ 3:13
□ ሴት ከሆንሽ “ጭምትና ገር መንፈስ” እንዳለሽ የምታሳዪው እንዴት ነው?—1 ጴጥሮስ 3:4
□ ልጆች ለመውለድ ታስባላችሁ? (መዝሙር 127:3) ካልሆነ ምን ዓይነት የወሊድ መቆጣጠሪያ ትጠቀማላችሁ?
□ ወንድ ከሆንህ የቤተሰብህን መንፈሳዊ ፍላጎት የማሟላት ኃላፊነትህን እንዴት ለመወጣት አስበሃል?—ማቴዎስ 5:3
ባሕርይ
□ ትጉህ ሠራተኛ መሆንህን እያሳየህ ያለኸው እንዴት ነው?—ምሳሌ 6:9-11፤ 31:17, 19, 21, 22, 27
□ የራስህን ጥቅም መሥዋዕት የምታደርግ ሰው እንደሆንህ እያሳየህ ያለኸው እንዴት ነው?—ፊልጵስዩስ 2:4
□ ወንድ ከሆንህ የራስነት ሥልጣንህን የምትጠቀምበት መንገድ የክርስቶስን ምሳሌ እንደምትከተል የሚያሳየው እንዴት ነው?—ኤፌሶን 5:25, 28, 29
□ ሴት ከሆንሽ ለሥልጣን መገዛት እንደማይከብድሽ በሕይወትሽ እያሳየሽ ነው?—ኤፌሶን 5:22-24
[በገጽ 219 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ጥልቀቱን የማታውቁት ውኃ ውስጥ ዘላችሁ እንደማትገቡ ሁሉ ስለ ትዳር በቂ እውቀት ሳይኖራችሁ ለማግባት አትቸኩሉ