ሃይማኖትን መቀላቀል
ሃይማኖት አለን የሚሉ ሰዎች ሁሉ የሚያመልኩት አንድ አምላክ ነው?
እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ትምህርቶችን እያስተማሩ ያሉት ሃይማኖቶች ሁሉ ይሖዋን ሊያስደስቱ ይችላሉ?
ማቴ 7:13, 14፤ ዮሐ 17:3፤ ኤፌ 4:4-6
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ኢያሱ 24:15—ኢያሱ፣ ከይሖዋ ወይም ከሌሎች አማልክት አንዱን ለማገልገል መምረጥ እንዳለባቸው ለሕዝቡ ነግሯቸዋል
-
1ነገ 18:19-40—ይሖዋ፣ እውነተኛውን አምላክ የሚያገለግሉ ሰዎች እንደ ባአል ላሉ የሐሰት አማልክት በሚቀርቡ የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ መካፈል እንደሌለባቸው በነቢዩ ኤልያስ አማካኝነት ተናግሯል
-
ይሖዋ ስለ ሐሰት አማልክት እንዲሁም ለእነሱ ስለሚቀርበው አምልኮ ምን ይሰማዋል?
ይሖዋ፣ ሰዎች እሱን እንደሚያመልኩ እየተናገሩ የአምልኮ ሥርዓቱን እሱ ከሚጠላው ነገር ጋር ሲቀላቅሉ ምን ይሰማዋል?
ኢሳ 1:13-15፤ 1ቆሮ 10:20-22፤ 2ቆሮ 6:14, 15, 17
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዘፀ 32:1-10—አሮን በእስራኤላውያን ወገኖቹ ተጽዕኖ ተሸንፎ የጥጃ ሐውልት ሠራ፤ ሕዝቡ “ለይሖዋ የሚከበር በዓል” በሚል ስም ጥጃውን ማምለካቸው ይሖዋን በጣም አስቆጥቶታል
-
1ነገ 12:26-30—ንጉሥ ኢዮርብዓም ሕዝቡ ለአምልኮ ኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ቤተ መቅደስ እንዲሄድ አልፈለገም፤ ይሖዋን ይወክላሉ በማለት ጣዖቶች ሠራ፤ ይህም ሕዝቡን ወደ ኃጢአት መርቶታል
-
ይሖዋ፣ ሌሎች አማልክትን ከሚያመልኩ ሰዎች ጋር ኅብረት መፍጠርን በተመለከተ እስራኤላውያንን ምን ብሏቸዋል?
ይሖዋ፣ አገልጋዮቹ ሌሎች ሃይማኖቶች በሚያደርጓቸው የአምልኮ ሥርዓቶች ላይ በመሳተፋቸው ምን ተሰምቶታል?
መሳ 10:6, 7፤ መዝ 106:35-40፤ ኤር 44:2, 3
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
1ነገ 11:1-9—ንጉሥ ሰለሞን በባዕድ አገር ሚስቶቹ ተጽዕኖ ተሸንፎ ጣዖት አምልኮን የሚያበረታታ ነገር በማድረጉ ይሖዋ ተቆጥቷል
-
መዝ 78:40, 41, 55-62—አሳፍ፣ እስራኤላውያን ማመፃቸውና ጣዖት ማምለካቸው ይሖዋን ምን ያህል እንዳሳዘነው ገልጿል፤ በኋላም ሕዝቡን እርግፍ አድርጎ እንዲተው እንዳስገደደው ተናግሯል
-
ኢየሱስ ከአምላክ ቃል ጋር የሚጋጩ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ደግፏል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 16:6, 12—ኢየሱስ የፈሪሳውያንንና የሰዱቃውያንን ትምህርት ከእርሾ ጋር አመሳስሎታል፤ ምክንያቱም የሐሰት ትምህርቶች በፍጥነት የሚሰራጩ ከመሆኑም ሌላ በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ንጹሕ እውነት ይበክላሉ
-
ማቴ 23:5-7, 23-33—ኢየሱስ የጸሐፍትንና የፈሪሳውያንን ግብዝነትና የሐሰት ትምህርቶቻቸውን አጥብቆ አውግዟል
-
ማር 7:5-9—ጸሐፍትና ፈሪሳውያን ወጎቻቸውን ከአምላክ ቃል እንዳስበለጡ ኢየሱስ አጋልጧል
-
ኢየሱስ ተከታዮቹ የየራሳቸውን ሃይማኖታዊ ቡድኖች እንዲያቋቁሙ አበረታቷቸዋል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ዮሐ 15:4, 5—ኢየሱስ የወይን ተክልን ምሳሌ አድርጎ በመጠቀም ተከታዮቹ ከእሱ ጋርም ሆነ ከእምነት አጋሮቻቸው ጋር አንድነት ሊኖራቸው እንደሚገባ አስተምሯል
-
ዮሐ 17:1, 6, 11, 20-23—ኢየሱስ ከመገደሉ በፊት ከሐዋርያቱ ጋር ባሳለፈው የመጨረሻ ምሽት እውነተኛ ተከታዮቹ በሙሉ አንድነት እንዲኖራቸው ጸልዮአል
-
በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት የክርስቲያን ጉባኤዎች የሚያምኑባቸው ነገሮች ተመሳሳይ ነበሩ? ይሖዋን የሚያመልኩበት መንገድስ?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ሥራ 11:20-23, 25, 26—በአንጾኪያ እና በኢየሩሳሌም የሚገኙት ጉባኤዎች አንድነት ነበራቸው፤ ተባብረው ይሠሩም ነበር
-
ሮም 15:25, 26፤ 2ቆሮ 8:1-7—በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ጉባኤዎች ለእርዳታ ሥራ በልግስና መዋጮ አድርገዋል፤ ይህም በጉባኤዎቹ መካከል የነበረውን ፍቅርና አንድነት የሚያሳይ ነው
-
አንድ ሃይማኖት በክርስቶስ አምናለሁ ስላለ ብቻ ሃይማኖቱ በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ይኖረዋል?
ሰዎች ከክርስቶስና ከሐዋርያት ትምህርቶች ካፈነገጡ አምልኳቸው ተቀባይነት ይኖረዋል?
-
ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦
-
ማቴ 13:24-30, 36-43—ኢየሱስ የእንክርዳድን ምሳሌ በመጠቀም ብዙ አስመሳይ ክርስቲያኖች በጉባኤው ውስጥ ብቅ እንደሚሉ ተናግሯል
-
1ዮሐ 2:18, 19—አረጋዊው ሐዋርያ ዮሐንስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን መጨረሻ ላይ ሲጽፍ ያኔም እንኳ ብዙ ፀረ ክርስቶሶች እንደተነሱ ተናግሯል
-
በጉባኤው ውስጥ የሐሰት ትምህርትና ክርስቲያናዊ ያልሆነ ምግባር በቸልታ ከታለፈ ምን ይፈጠራል?
ክርስቲያኖች አንድነታቸውን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይኖርባቸዋል?
ክርስቲያኖች ከሐሰት አምልኮ ጋር ንክኪ ሊኖራቸው የማይገባው ለምንድን ነው?
ሐሰት የሆኑ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ማጋለጥ ተገቢና ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
እውነተኛውን አምልኮ የሚቃወሙ ሰዎች ጥቃት ቢሰነዝሩብንና ቢያሳድዱን ልንገረም የማይገባው ለምንድን ነው?