በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጥፎ ልማዶች

መጥፎ ልማዶች

ክርስቲያኖች የትኞቹን መጥፎ ልማዶች ሊያስወግዱ ይገባል?

ሆዳምነት

ምሳሌ 23:20, 21፤ 28:7

በተጨማሪም ሉቃስ 21:34, 35⁠ን ተመልከት

ሐሜት፤ በሌሎች ጉዳይ ጣልቃ መግባት

መረን የለቀቀ ፈንጠዝያ

ሮም 13:13፤ ገላ 5:19, 21፤ 1ጴጥ 4:3

በተጨማሪም ምሳሌ 20:1፤ 1ቆሮ 10:31⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዳን 5:1-4, 30—ንጉሥ ቤልሻዛር ያዘጋጀው “ታላቅ ግብዣ” ከልክ በላይ ወደ መጠጣትና ይሖዋን ወደ መሳደብ መርቶታል፤ ይህም ጥፋት አምጥቶበታል

ማንአለብኝነት፤ ርኩሰት፤ የፆታ ብልግና፤ ምንዝር

የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት

ማጉረምረም

1ቆሮ 10:10፤ ፊልጵ 2:14፤ ይሁዳ 16

በተጨማሪም ዘኁ 11:1⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘኁ 14:1-11, 26-30—እስራኤላውያን በሙሴና በአሮን ላይ አጉረመረሙ፤ ይሖዋ ግን በእሱ ላይ እንዳጉረመረሙ አድርጎ ቆጥሮታል

    • ዮሐ 6:41-69—አይሁዳውያን በኢየሱስ ላይ አጉረመረሙ፤ አንዳንድ ደቀ መዛሙርቱም ትተውት ሄዱ

ስርቆት

ስርቆት” የሚለውን ተመልከት

ስካር፤ ከልክ በላይ መጠጣት

ምሳሌ 20:1፤ 23:20, 29-35፤ 1ቆሮ 5:11፤ 6:9, 10

በተጨማሪም ኤፌ 5:18፤ 1ጢሞ 3:8ቲቶ 2:3፤ 1ጴጥ 4:3⁠ን ተመልከት

በተጨማሪም “መጠጣት” የሚለውን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 9:20-25—ኖኅ መስከሩ፣ ካም እና ልጁ ከነአን ከባድ ኃጢአት እንዲሠሩ መንገድ ከፍቷል

    • ዳን 5:1-6, 30—ንጉሥ ቤልሻዛር ብዙ ጠጥቶ ሞቅ ሲለው ይሖዋን ሰደበ፤ ይህም በእሱም ሆነ በመንግሥቱ ላይ ጥፋት አምጥቷል

ስድብ

ማቴ 5:22፤ 1ቆሮ 6:9, 10፤ ኤፌ 4:31

በተጨማሪም ዘፀ 22:28፤ መክ 10:20ይሁዳ 8⁠ን ተመልከት

ሽንገላ

ኢዮብ 32:21, 22፤ መዝ 5:9፤ 12:2, 3፤ ምሳሌ 26:24-28፤ 29:5

በተጨማሪም ምሳሌ 28:23፤ 1ተሰ 2:3-6⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሉቃስ 18:18, 19—ኢየሱስ በሽንገላ የተሰጠውን የማዕረግ ስም አልተቀበለም

    • ሥራ 12:21-23—ንጉሥ ሄሮድስ አግሪጳ፣ ሕዝቡ ‘አምላክ ነው’ እያሉ ሲያሞካሹት ሽንገላውን በመቀበሉ ተቀስፎ ሞቷል

ቅሚያ፤ ዝርፊያ

መዝ 62:10፤ 1ቆሮ 5:10, 11፤ 6:9, 10

በተጨማሪም ምሳሌ 1:19፤ 15:27⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ኤር 22:11-17—ንጉሥ ሻሉም (ኢዮአካዝ) ቅሚያና ሌሎች ከባድ ኃጢአቶች በመፈጸሙ ይሖዋ አውግዞታል

    • ሉቃስ 19:2, 8—የቀረጥ ሰብሳቢዎች አለቃ የሆነው ዘኬዎስ ከሰዎች በመቀማት ለፈጸመው ኃጢአት ንስሐ ገብቷል፤ ተበዳዮቹን ለመካስም ቃል ገብቷል

    • ሥራ 24:26, 27—አገረ ገዢው ፊሊክስ፣ ጳውሎስ ጉቦ ይሰጠኛል ብሎ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም ሐዋርያው አልሰጠውም

ነፍስ ማጥፋት

ዘፀ 20:13፤ ማቴ 15:19፤ 1ጴጥ 4:15

በተጨማሪም ማቴ 5:21, 22፤ ማር 7:21⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፍ 4:4-16—ቃየን፣ ይሖዋ በፍቅር የሰጠውን ምክር አልቀበልም ብሎ ጻድቅ የሆነውን ወንድሙን አቤልን ገድሎታል

    • 1ነገ 21:1-26፤ 2ነገ 9:26—ክፉው ንጉሥ አክዓብና ንግሥት ኤልዛቤል በስግብግብነት ተነሳስተው የናቡቴና የልጆቹ ሕይወት እንዲጠፋ አድርገዋል

ክፍፍል መፍጠር፤ ኑፋቄ ማስፋፋት

ውሸት፤ ስም ማጥፋት

ውሸት” የሚለውን ተመልከት

ውሸት፤ ቃል ማፍረስ

ውሸት” የሚለውን ተመልከት

ዛቻ

ኤፌ 6:9፤ 1ጴጥ 2:23

በተጨማሪም መዝ 10:4, 7፤ 73:3, 8⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ሥራ 4:15-21—የሳንሄድሪን ሸንጎ፣ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የስብከቱን ሥራ እንዳያከናውኑ ለማስቆም በማሰብ ዛቻ ሰንዝሮባቸዋል

ደምን አላግባብ መጠቀም

ዘፍ 9:4፤ ዘዳ 12:16, 23፤ ሥራ 15:28, 29

በተጨማሪም ዘሌ 3:17፤ 7:26⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 14:32-34—እስራኤላውያን የእንስሳውን ደም በአግባቡ ሳያፈስሱ ሥጋውን በመብላት በይሖዋ ላይ ኃጢአት ሠሩ

ጉራ

ጉራ” የሚለውን ተመልከት

ጉቦ መስጠት ወይም መቀበል

ዘፀ 23:8፤ መዝ 26:9, 10፤ ምሳሌ 17:23

በተጨማሪም ዘዳ 10:17፤ 16:19መዝ 15:1, 5⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 1ሳሙ 8:1-5—የነቢዩ ሳሙኤል ልጆች የአባታቸውን ግሩም ምሳሌ ከመከተል ይልቅ ጉቦ ይቀበሉና ፍትሕ ያዛቡ ነበር

    • ነህ 6:10-13—በተቃዋሚዎች የተቀጠረው ሸማያህ የሐሰት ትንቢት ተናግሯል፤ እንዲህ ያደረገው አገረ ገዢውን ነህምያን ለማስፈራራትና የይሖዋን ሥራ ለማዘግየት ብሎ ነው

ጠብ

ጠብ” የሚለውን ተመልከት

ጣዖት አምልኮ

ጣዖት አምልኮ” የሚለውን ተመልከት

ጥል፤ ዓመፅ

መዝ 11:5፤ ምሳሌ 3:31፤ 29:22

በተጨማሪም 1ጢሞ 3:2, 3፤ ቲቶ 1:7⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ዘፀ 21:22-27—በሙሴ ሕግ መሠረት ሁለት ሰዎች ሲደባደቡ በሌላ ሰው ላይ ጉዳት ወይም ሞት ካስከተሉ ቅጣት ይጣልባቸዋል

ጸያፍ ንግግር ወይም ቀልድ

ኤፌ 5:4፤ ቆላ 3:8

በተጨማሪም ኤፌ 4:29, 31⁠ን ተመልከት

ፉክክር

መክ 4:4፤ ገላ 5:26

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • ማር 9:33-37፤ 10:35-45—ሐዋርያት ትልቅ ቦታ ለማግኘት የመፎካከር ልማድ ስለነበራቸው ኢየሱስ በተደጋጋሚ እርማት ሰጥቷቸዋል

    • 3ዮሐ 9, 10—ዲዮጥራጢስ በወንድሞች መሃል “የመሪነት ቦታ መያዝ” ይፈልግ ነበር

ፌዝ

ምሳሌ 19:29፤ 24:9

በተጨማሪም ምሳሌ 17:5፤ 22:102ጴጥ 3:3, 4⁠ን ተመልከት

  • ጠቃሚ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች፦

    • 2ዜና 36:15-21—ዓመፀኛ የሆኑት የአምላክ ሕዝቦች በመልእክተኞቹ ላይ በማፌዛቸውና በነቢያቱ ላይ በማላገጣቸው ከባድ ቅጣት ደርሶባቸዋል

    • ኢዮብ 12:4፤ 17:2፤ 21:3፤ 34:7—ጻድቁ ኢዮብ ከባድ ፈተና ውስጥ በነበረበት ወቅት ሰዎች አፊዘውበታል

ፖርኖግራፊ

ፖርኖግራፊ” የሚለውን ተመልከት