አምላክ ያስብልሃል
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ስለሆነ ከሁሉ የተሻለ ምክር ይሰጠናል። መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ ባይሆንም አስጨናቂ ሁኔታዎችን፣ የሚረብሹ ሐሳቦችን፣ መጥፎ ስሜቶችንና የአካልም ሆነ የአእምሮ ሕመሞችን ለመቋቋም ይረዳናል።
ከሁሉ በላይ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ፈጣሪያችን ይሖዋ አምላክ a አስተሳሰባችንንና ስሜታችንን ከማንም በተሻለ እንደሚረዳልን ዋስትና ይሰጠናል። አምላካችን የሚያጋጥመንን ማንኛውንም ችግር እንድንቋቋም ሊረዳን ዝግጁ ነው። የሚያጽናኑ ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን እንደ ምሳሌ እንውሰድ፦
“ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤ መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውንም ያድናል።”—መዝሙር 34:18
“‘አትፍራ። እረዳሃለሁ’ የምልህ እኔ፣ አምላክህ ይሖዋ ቀኝ እጅህን ይዣለሁ።”—ኢሳይያስ 41:13
ይሁንና ይሖዋ ከአእምሮ ጤንነት ጋር የተያያዙ ችግሮችን እንድንቋቋም የሚረዳን እንዴት ነው? በቀጣዮቹ ርዕሶች ላይ እንደምንመለከተው ይሖዋ በተለያዩ መንገዶች እንደሚያስብልን ያሳየናል።
a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18