በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“መንግሥትህ ትምጣ”—የብዙዎች ጸሎት

“መንግሥትህ ትምጣ”—የብዙዎች ጸሎት

“መንግሥትህ ትምጣ” ብለህ ጸልየህ ታውቃለህ? ባለፉት መቶ ዘመናት ሁሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ይህን ጸሎት ሲጸልዩ ኖረዋል። እንዲህ ብለው የሚጸልዩት ለምንድን ነው? ኢየሱስ ተከታዮቹን “መንግሥትህ ትምጣ” ብለው እንዲጸልዩ ስላስተማረ ነው።

የኢየሱስ ተከታዮች ኢየሱስ ስለ አምላክ መንግሥት ከተናገራቸው ነገሮች መካከል አንዳንዶቹን መጀመሪያ ላይ አልተረዷቸውም ነበር። እንዲያውም በአንድ ወቅት “ጌታ ሆይ፣ ለእስራኤል መንግሥትን መልሰህ የምታቋቁመው በዚህ ጊዜ ነው?” በማለት ጠይቀውት ነበር። ኢየሱስ ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አለመስጠቱ አስገርሟቸው መሆን አለበት። (የሐዋርያት ሥራ 1:6, 7) ታዲያ የአምላክ መንግሥት ምን እንደሆነና መቼ እንደሚመጣ ማወቅ አይቻልም ማለት ነው? በፍጹም!

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ እንድታገኝ ይረዳሃል፦

  • የአምላክ መንግሥት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

  • የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ማን ነው?

  • የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?

  • የአምላክ መንግሥት ምን ነገሮችን ያከናውናል?

  • የአምላክን መንግሥት ለመደገፍ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ ያለብን ለምንድን ነው?

  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?