በትምህርት ቤት ላቀረበችው ሪፖርት ጠቅሟታል
በትምህርት ቤት ላቀረበችው ሪፖርት ጠቅሟታል
በጀርመን በሚገኝ አንድ የሙያ ትምህርት ቤት ውስጥ በርካታ የውጪ አገር ተማሪዎች ይማራሉ። ተማሪዎቹ ከሊባኖስ፣ ከሕንድ፣ ከሩሲያ፣ ከዩክሬን፣ ከቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከጆርጂያ፣ ከፈረንሳይ፣ ከፖላንድና ከቬትናም የመጡ ናቸው።
ከተማሪዎቹ መካከል አንዷ እንዲህ ስትል ጽፋለች:- “በትምህርት ቤት ሪፖርት ማቅረብ የምንችልበት አጋጣሚ ሲመጣ ሪፖርቱን ለማቅረብ ፈቃደኛ ሆንኩ። ለሪፖርቱ የመረጥኩት ርዕስ ‘ወጣቶች ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች’ የሚል ሲሆን ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች በተባለው መጽሐፍ ላይ የተመሠረተ ነበር። ተማሪዎቹ በመጽሐፉ ውስጥ በተካተቱት ርዕሶችና ውስጡ በቀረቡት ሐሳቦች ተገርመው ነበር።
“ሪፖርቱን አቅርቤ ስጨርስ ተማሪዎቹ ሞቅ ባለ ጭብጨባ አድናቆታቸውን ገለጹ። ሁሉም የቋንቋ ተማሪዎች ስለነበሩና እንግሊዝኛ በደንብ ስለሚረዱ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የሚለውን መጽሐፍ 30 ቅጂ ማበርከት ችያለሁ፤ ለአስተማሪዬ ደግሞ በጀርመንኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን ሰጠኋት።”
በቀጣዮቹ ቀናት ይህቺ ተማሪ አብረዋት ከሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች ጋር ውይይት የቀጠለች ሲሆን ተማሪዎቹም ጥሩ ፍላጎት አሳይተዋል። ለእነዚህ ተማሪዎች በቤንጋሊ፣ በስፓንኛና በአረብኛ እንዲሁም በሩሲያ፣ በጆርጂያ፣ በፖላንድና በቬትናም ቋንቋዎች የተዘጋጁ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሌሎች ጽሑፎችን ሰጥታቸዋለች።
ምናልባት አንተም ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ከተባለው መጽሐፍ ጥቅም ሊያገኝ የሚችል ወጣት ታውቅ ይሆናል። መጽሐፉ ካካተታቸው 39 ምዕራፎች ውስጥ “እውነተኛ ጓደኞች ላፈራ የምችለው እንዴት ነው?፣” “ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት ቢፈጸም ምናለበት?፣” እንዲሁም “እውነተኛ ፍቅር መሆን አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ?” የሚሉት ይገኙበታል። ይህን መጽሐፍ ማግኘት የምትፈልግ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተህ በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ትችላለህ።
□ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።