በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለምታምንበት ነገር ጠንካራ አቋም ይዛለች

ለምታምንበት ነገር ጠንካራ አቋም ይዛለች

ለምታምንበት ነገር ጠንካራ አቋም ይዛለች

የአንደኛ ክፍል ተማሪና የሰባት ዓመት ልጅ የሆነችው ሞርገን፣ በገና በዓል ሰሞን ስለ ገና በዓል የሚናገር ታሪክ እንድታነብ ተመደበች። በዚህ ጊዜ ሞርገን ወደ አስተማሪዋ ሄዳ ይህ በዓል ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር እንደሚጋጭ እንደሚሰማት ነገረቻት። አስተማሪዋም ሕሊናዋን የማይረብሽ ሌላ ታሪክ እንድታነብ በደግነት ፈቀደችላት።

ከጊዜ በኋላ የሞርገን ቤተሰቦች በትምህርት ቤቱ የሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኙ ተጋበዙ። ሞርገን ለምታምንበት ነገር ጠንካራ አቋም በመያዝ ባሳየችው ድፍረት ምክንያት በሥነ ሥርዓቱ ላይ ሽልማት ሲሰጣት በጣም ተገረመች። እንዲህ ያለውን ድፍረት ልታዳብር የቻለችው እንዴት እንደሆነ ስትጠየቅ ከታላቁ አስተማሪ ተማር የተባለውን መጽሐፍ ከቤተሰቧ ጋር ሆና እንደምታነብ ተናገረች፤ እንዲሁም በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት ትምህርቶች የተወሰዱት ኢየሱስ ክርስቶስ ካሳለፈው ሕይወትና ከሰጣቸው ትምህርቶች ላይ መሆኑን አብራራች።

ውብ ሥዕሎችን የያዘው ይህ ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ውይይት እንዲያደርጉ ይረዳቸዋል። “መዋሸት የሌለብን ለምንድን ነው?” “ሁሉም ዓይነት ግብዣ አምላክን ያስደስተዋል?” እንዲሁም “ያለብንን ፍርሃት ለማሸነፍ የሚያስችል እርዳታ” እንደሚሉት ያሉ ርዕሶችን የሚያብራሩ ምዕራፎችንም ይዟል።

እርስዎም ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ አለዚያም ደግሞ በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።

❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።

❑ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።