በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ጥሩ ውሳኔ ነበር?

ዘፍጥረት 39:1-23ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ።

1. በዚህ ሥዕል ላይ የምትታየው ሴት ማን ነች?

․․․․․

2. ሰውየውስ ማን ነው?

․․․․․

3. ሰውየው ምን ዓይነት ውሳኔ አደረገ?

․․․․․

ለውይይት፦

ሰውየው ይህን ውሳኔ ያደረገው ለምንድን ነው? በዚህ ምክንያትስ የደረሰበት ችግር ነበር? ትክክለኛ ውሳኔ ያደረገ ይመስልሃል? አድርጓል ካልክ ለምን? ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ በመወሰንህ ችግር ሊያጋጥምህ የሚችለው መቼ ሊሆን ይችላል?

ስለ ንጉሥ ሳኦል ምን የምታውቀው ነገር አለ?

4. ሳኦል ምን ዓይነት የሰውነት አቋም ነበረው?

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 9:1, 2ን አንብብ።

․․․․․

5. ይሖዋ ሳኦልን የተወው ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 13:13, 14ን አንብብ።

․․․․․

ለውይይት፦

ከአንድ ሰው አካላዊ ቁመና ይበልጥ አምላክ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምኑ ነው? ፍንጭ፦ 1 ሳሙኤል 16:6, 7ን አንብብ። ይህን ሐቅ ማወቅህ ስለ አካላዊ ቁመናህ ሚዛናዊ አመለካከት እንድትይዝ የረዳህ እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ 1 ጢሞቴዎስ 4:8ን አንብብ።

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

ከዚህ እትም

የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ፤ እንዲሁም የጎደለውን ቁጥር አሟላ።

ገጽ 4 መጽሐፍ ቅዱስ ሥራን በተመለከተ ምን ማበረታቻ ይዟል? መክብብ 3:․․․

ገጽ 7 የምንሠራው ለምን መሆን አለበት? ዮሐንስ 6:․․․

ገጽ 10 አምላክ ምን ለማድረግ ቀን ወስኗል? የሐዋርያት ሥራ 17:․․․

ገጽ 28 አንድ ወንድና ሴት ሲጋቡ ምን ይሆናሉ? ዘፍጥረት 2:․․․

● መልሱ በገጽ 14 ላይ ይገኛል

በገጽ 31 ላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች

1. የጲጥፋራ ሚስት።

2. ዮሴፍ።

3. ከጲጥፋራ ሚስት ጋር ላለመተኛት።

4. ሳኦል ቁመቱ ረጅምና መልከ ቀና ነበር።

5. ሳኦል አምላክን አልታዘዘም።