“ታላቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራ”
“ታላቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራ”
● ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት እንዲሁም በሕይወታችን ላይ በጎ ተጽዕኖ ስለሚያሳድሩት ትምህርቶቹ እና የማይረሱ ምሳሌዎቹ ማወቅ ትፈልጋለህ? ከሆነ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው የተባለውን መጽሐፍ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
አንድ ሰው ይህን መጽሐፍ ካነበበ በኋላ እንዲህ በማለት አድናቆቱን ገልጿል፦ “ቀለል ባለ መንገድ የተጻፈ ቢሆንም ጌታችን ምድር በነበረበት ጊዜ ያሳለፈውን ሕይወት ማራኪ በሆነ መንገድ በዝርዝር የሚተርክ ታላቅ የሥነ ጽሑፍ ሥራ ነው።”
በመጽሐፉ ላይ ያሉት ክንውኖች በተቻለ መጠን የጊዜ ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው የተጻፉ ናቸው። ይህ መጽሐፍ የተመሠረተው በኢየሱስ ዘመን የነበሩት ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ የተባሉ አራት የወንጌል ጸሐፊዎች በአምላክ መንፈስ መሪነት በጻፏቸው መጻሕፍት ላይ ነው። ማቴዎስና ዮሐንስ፣ ሐዋርያት ሲሆኑ ከኢየሱስ ጋር አብረው ተጉዘዋል። ማርቆስ የኢየሱስ ሐዋርያ የነበረው የጴጥሮስ የቅርብ ጓደኛ ነበር። ሐኪሙ ሉቃስ ደግሞ የሐዋርያው ጳውሎስ የጉዞ ጓደኛ ነበር።
ይህን መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
❑ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።