ልጃችሁን ማስተማር መጀመር ያለባችሁ መቼ ነው?
ልጃችሁን ማስተማር መጀመር ያለባችሁ መቼ ነው?
● በሳውዝ ካሮላይና፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በምትገኝ ሰመርቪል በተባለች ከተማ የሚኖር አንድ ሰው፣ ባለቤቱ የሦስት ወር ነፍሰ ጡር ከነበረችበት ጊዜ አንስቶ በየቀኑ ማታ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ የተባለውን መጽሐፍ ወደ እሷ ተጠግቶ ለሕፃኗ ያነብ እንደነበር ጽፏል። ይህ አባት እንዲህ ሲል ተናግሯል፦ “ትንሿ ልጃችን ቤታያ ከተወለደች በኋላም ይህንኑ ልማዳችንን በመቀጠል መጽሐፉን ሦስት ጊዜ አንብበን እስክንጨርስ ድረስ በየቀኑ ማታ ላይ ከመጽሐፉ አንድ ታሪክ እናነብላት ነበር።”
አክሎም እንዲህ ብሏል፦ “ቤታያ አፍ በፈታችበት ወቅት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን አብዛኞቹን ባለታሪኮች ታውቃቸው የነበረ ከመሆኑም ሌላ በመጽሐፉ ውስጥ ያሉትን በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በድራማ መልክ መሥራት ችላ ነበር። ከዚህም ሌላ ቤታያ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን በቃሏ መናገር ችላለች።”
ማራኪ ሥዕሎች ባሉት በዚህ መጽሐፍ ላይ ያሉት 116 ታሪኮች የተጻፉት ባለታሪኮቹ በኖሩበት ዘመን ቅደም ተከተል በመሆኑ አንባቢው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ታሪኮች ስለተፈጸሙበት የጊዜ ቅደም ተከተል የበለጠ እውቀት ማግኘት ይችላል። ይህን ባለ 256 ገጽ መጽሐፍ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
❑ እዚህ ላይ የሚታየውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
❑ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።