ንቁ! ነሐሴ 2014 | ሰላም መፍጠር የሚቻለው እንዴት ነው?

ብዙ ሰዎች ከጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም መኖር ይፈልጋሉ፤ ይሁንና በውስጣችን ያሉትን መጥፎ ባሕርያት ማሸነፍና ስሜታችንን የጎዳንን ሰው ይቅር ማለት ከባድ ሊሆንብን ይችላል። አለመግባባቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍታት የሚቻለው እንዴት ነው?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ሰላም መፍጠር የሚቻለው እንዴት ነው?

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ መመሪያዎች ቀደም ሲል ጠላት የነበሩ ሰዎች ሰላም እንዲፈጥሩና ወዳጆች እንዲሆኑ አስችለዋቸዋል።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ የመማሪያ መጻሕፍት መተካታቸው፣ አካባቢ እንደማይበክል የሚታሰብ የነዳጅ ዓይነት የአየር ብክለት ማስከተሉ እና የአንድ ክርስትና ሃይማኖት አብዛኞቹ አባላት መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው የማያውቁ መሆናቸው።

ለቤተሰብ

“አይሆንም” ማለት የምትችሉት እንዴት ነው?

ልጃችሁ በማልቀስ ወይም በመለማመጥ ውሳኔያችሁን እንድትቀይሩ ቢፈታተናችሁ ምን ታደርጋላችሁ?

‘ወፎችን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ’

ኢየሱስ ይህን ሐሳብ የተናገረው ምን ትምህርት ለማስተላለፍ ፈልጎ ነው?

የታሪክ መስኮት

ዊልያም ዊስተን

‘የተከበረው ምሁር ከምሁራኑ ማኅበረሰብ ተገለለ’—ግን ለምን?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ከአምላክ የመጡ ሕልሞች

በዛሬው ጊዜ አምላክ ለሰዎች መልእክት ለማስተላለፍ በሕልም ይጠቀማል?

ንድፍ አውጪ አለው?

ብርሃን የመሰብሰብ ችሎታ ያለው የቢራቢሮ ክንፍ

አንዳንድ የቢራቢሮ ዝርያዎች ይህ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረገው ክንፋቸው ጥቁር መሆኑ ብቻ አይደለም።

በተጨማሪም . . .

ወጣቶች ስለ ጤናማ አኗኗር የሰጡት ሐሳብ

ተገቢ አመጋገብ እንዲኖርህ ማድረግና ስፖርት መሥራት ይከብድሃል? አንዳንድ ወጣቶች ጤንነታቸው ለመጠበቅ ምን እንደሚያደርጉ በዚህ ክሊፕ ላይ ተናግረዋል።

ፈርዖን የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ

የግብፅ ሠራዊት ቀይ ባሕር ውስጥ በሰጠመበት ወቅት ፈርዖን ተርፏል?