መጠበቂያ ግንብ—የጥናት እትም ጥቅምት 2012

ይህ እትም የሚያጋጥሙንን መከራዎች እንዴት መቋቋም እንደምንችል፣ ክርስቲያኖች የትኞቹን ባሕርያትና ድርጊቶች ማስወገድ እንዳለባቸውና አምላክ ከገባው ቃል ተጠቃሚ ለመሆን ምን ማድረግ እንዳለብን ያብራራል።

ራሳቸውን በፈቃደኝነት አቅርበዋል​—ብራዚል

አምላክን ይበልጥ በተሟላ ሁኔታ ለማገልገል ሲሉ ወደ ሌላ አካባቢ የተዛወሩ የአንዳንድ ክርስቲያኖችን አበረታች ተሞክሮ አንብብ።

በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥሙንን መከራዎች በድፍረት መቋቋም

ምንም ዓይነት መከራ ቢደርስብን ደፋሮች መሆንና ገንቢ በሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር የምንችለው እንዴት ነው?

የምታሳዩት መንፈስ ምን ዓይነት ነው?

ከሌሎች ጋር ምንጊዜም ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖረን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ጥሩ ወይም መጥፎ ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችን ታሪክ ይዟል። ከእነዚህ ታሪኮች ትምህርት ማግኘት ትችላለህ።

የሕይወት ታሪክ

ወዳጅነታችን 60 ዓመታት ቢያስቆጥርም ገና መጀመሩ ነው

እውነተኛ ጓደኝነት ስለመሠረቱ አራት የሙሉ ጊዜ አገልጋዮች የሚናገረውን ይህን የሕይወት ታሪክ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

አምላክን በመታዘዝ በመሐላ ከገባው ቃል ተጠቃሚ ሁኑ

አምላክ ከሰጣቸው ተስፋዎች፣ በመሐላ ከገባው ቃልና ከሰዎች ጋር ከገባቸው ቃል ኪዳኖች ምን ትምህርት ማግኘት እንችላለን?

ቃላችሁ አዎ ከሆነ አዎ ይሁን

እውነተኛ መሆን ሲባል ምንን ይጨምራል? ለአምላክ የገባነውን የላቀ ክብደት የሚሰጠው ቃል መጠበቅ የምንችለው እንዴት ነው?

‘ከሕፃናት አፍ’ የተገኘ ማበረታቻ

በሩሲያ የሚኖሩ ልጆች ክርስቲያን የሆኑ ጓደኞቻቸው ባደረጉላቸው ነገር እንዴት እንደተበረታቱ የሚገልጸውን ይህን ታሪክ አንብብ።