ኤደን ገነት የጠፋችው እንዴት ነው?
ለወጣት አንባቢያን
ኤደን ገነት የጠፋችው እንዴት ነው?
መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።
ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።—ዘፍጥረት 3:1-24ን አንብብ።
ሔዋን እባቡ ሲያናግራት መጀመሪያ ላይ ምን የተሰማት ይመስልሃል?
․․․․․
ከቁጥር 7-10 ላይ እንደተገለጸው አዳምና ሔዋን በወቅቱ ምን የተሰማቸው ይመስልሃል? (ኃጢአት የሠሩት ሆን ብለው እንደሆነ አስታውስ።)
․․․․․
ከቁጥር 22-24 ላይ በተገለጸው መሠረት አዳምና ሔዋን ከኤደን ገነት በተባረሩበት ጊዜ የነበረውን ሁኔታ እንዴት ትገልጸዋለህ?
․․․․․
ጥልቅ ምርምር አድርግ።
ሔዋን ዓይኗ ለውድቀት የዳረጋት እንዴት ነው? (ቁጥር 6ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
ሔዋን ፍሬውን ለመብላት ‘የጓጓችው’ ለምንድን ነው? (ቁጥር 4 እና 5ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
አዳም ከሔዋን ጋር በኃጢአቷ እንዲተባበር ያነሳሳው ምን ሊሆን ይችላል? (ቁጥር 6ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
ኃጢአት፣ ከአዳምና ሔዋን በኋላ ባሉት ትውልዶች ውስጥ በወንዶችና በሴቶች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ምን መጥፎ ውጤት አስከትሏል? (ቁጥር 16ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
አዳምና ሔዋን ኃጢአት በመሥራታቸው የተነሳ በመካከላቸው ያለው ግንኙነት እንደሻከረ የሚያሳየው ምንድን ነው? (ቁጥር 12ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
ይሖዋ ዓላማውን ከግቡ ለማድረስ ሲል ለችግሩ ወዲያው መፍትሔ ያዘጋጀው እንዴት ነው? (ቁጥር 15ን በድጋሚ አንብብ።)
․․․․․
ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለተዘረዘሩት ነገሮች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦
በራስ የመመራት መንፈስ ስላለው አደጋ።
․․․․․
ዓይን መጥፎ ምኞቶች እንዲያድሩብን የሚያደርግ ስለመሆኑ።
․․․․․
የሠራነውን ስህተት በሌሎች ማሳበብ ጥቅም የሌለው ስለመሆኑ።
․․․․․
ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?
․․․․․