በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የተሳሳተ ትምህርት 4፦ አምላክ ሥላሴ ነው

የተሳሳተ ትምህርት 4፦ አምላክ ሥላሴ ነው

ይህ የተሳሳተ ትምህርት የመነጨው ከየት ነው?

“ካሉት መረጃዎች አንጻር የሥላሴ ቀኖና በ4ኛው መቶ ዘመን ማብቂያ ላይ የተፈጠረ ትምህርት እንደሆነ መደምደም ይቻላል። በአንድ በኩል ሲታይ ይህ መደምደሚያ እውነት ነው፤ . . . ‘አንድ አምላክ በሦስት አካላት’ የሚለው ድንጋጌ ጠንካራ መሠረት ያገኘውና በክርስትና ሕይወት ብሎም ሃይማኖታዊ እምነት ውስጥ ሙሉ በሙሉ የተዋሃደው ከ4ኛው መቶ ዘመን በኋላ ነበር።”—ኒው ካቶሊክ ኢንሳይክሎፒዲያ (1967)፣ ጥራዝ 14፣ ገጽ 299

“የኒቂያ ጉባኤ የተካሄደው ግንቦት 20, 325 [ዓ.ም.] ነበር። የስብሰባው ሊቀ መንበር ቆስጠንጢኖስ ራሱ ሲሆን ውይይቱን በመምራት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፤ ከዚህም በላይ ጉባኤው ባስተላለፈው ድንጋጌ ላይ የሚገኘውን ክርስቶስ ከአምላክ ጋር ስላለው ዝምድና ማለትም ‘ከአብ ጋር አንድ አካል ስለመሆኑ’ የሚገልጸውን ወሳኝ ሐሳብ ያቀረበው እሱ ራሱ . . . ነው። . . . ከሁለቱ በስተቀር ጳጳሳቱ በሙሉ ንጉሠ ነገሥቱን በመፍራት እንዲያውም አብዛኞቹ አለፍላጎታቸው ድንጋጌውን በፊርማቸው አረጋገጡ።”—ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ (1970)፣ ጥራዝ 6፣ ገጽ 386

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“እስጢፋኖስ ግን በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኩር ብሎ ሲመለከት፣ የእግዚአብሔርን ክብር፣ እንዲሁም ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፣ ‘እነሆ፤ ሰማያት ተከፍተው፣ የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ’ አለ።”—የሐዋርያት ሥራ 7:55, 56 አ.መ.ት

እስጢፋኖስ የተመለከተው ነገር ምን ያስገነዝበናል? እስጢፋኖስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ኢየሱስን “በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ” ተመልክቶታል። ከዚህ በግልጽ መመልከት እንደሚቻለው ኢየሱስ ከሞት ተነስቶ ወደ ሰማይ ከሄደ በኋላ እግዚአብሔር አልሆነም፤ ከዚህ ይልቅ ከእግዚአብሔር የተለየ መንፈሳዊ አካል ሆኗል። በዚህ ዘገባ ላይ ከእግዚአብሔር ጎን ሌላ ሦስተኛ አካል እንዳለ አልተጠቀሰም። የሥላሴን መሠረተ ትምህርት የሚደግፍ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ለማግኘት ጥረት ቢደረግም የዶሚኒካን ነዋሪ የሆኑት ማሪ ኤሚል ቡዋማር የተባሉ ቄስ እንደጻፉት “በአንድ አምላክ ውስጥ ሦስት አካል . . . አለ የሚለውን ሐሳብ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በየትም ቦታ ላይ ማግኘት አይቻልም።”—አ ለኦብ ዱ ክሪስቲያኒዝም—ላ ኔሶንስ ዴ ዶግም (በክርስትና አጥቢያ ላይ—የቀኖናዎች መፈጠር)

ቆስጠንጢኖስ የሥላሴ ትምህርት እንዲስፋፋ ያደረገበት ምክንያት በአራተኛው መቶ ዘመን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የነበረውን የጦፈ ክርክር ለማስቆም ነበር። ይሁን እንጂ ይህ ትምህርት ሌላ ጥያቄ አስነስቷል፦ ኢየሱስን የወለደችው ማሪያም “ወላዲተ አምላክ” ወይም “የአምላክ እናት” ናት?

እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች አወዳድር፦ ማቴዎስ 26:39፤ ዮሐንስ 14:28፤ 1 ቆሮንቶስ 15:27, 28፤ ቆላስይስ 1:15, 16

እውነታው፦

የሥላሴ ቀኖና በ4ኛው መቶ ዘመን ማብቂያ ላይ የተፈጠረ ትምህርት ነው