በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ምድር የተፈጠረችው በዓላማ ነው?

ምድር የተፈጠረችው ለሰው ልጆች አስደሳች መኖሪያ እንድትሆን ነው

ምድር ሕይወትን ለማኖር ፍጹም ተስማሚ ናት። ለሕይወት በጣም አስፈላጊ የሆነው ውኃ ምድር ላይ በብዛት ይገኛል። የምድር ጋደል ያለ አቀማመጥ እንዲሁም በራሷ ዛቢያ ላይም ሆነ በፀሐይ ዙሪያ መሽከርከሯ ውቅያኖሶች ቀዝቅዘው ወደ በረዶነት እንዳይለወጡ በሌላ በኩል ደግሞ ተነው እንዳያልቁ ለመከላከል ይረዳሉ። እንዲሁም የምድር ከባቢ አየርና መግነጢሳዊ መስክ ምድርን አደገኛ ከሆነ ጨረር ይጠብቋታል። በምድር ላይ ያለው እርስ በርስ የተሳሰረ የዕፅዋትና የእንስሳት ሕይወትም ቢሆን በጣም አስደናቂ ነው። በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ምድር የተፈጠረችው በዓላማ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል።—ኢሳይያስ 45:18ን አንብብ።

ይሁን እንጂ ‘መከራና የፍትሕ መጓደል የዚህ ዓላማ ክፍል ናቸው?’ ብለህ ታስብ ይሆናል።—ዘዳግም 32:4, 5ን አንብብ።

ለምድር የታሰበው ዓላማ ይፈጸም ይሆን?

ምድር የተፈጠረችው እርስ በርሳቸው ለሚከባበሩና ፈጣሪያቸውን ለሚወዱ ሰዎች አስደሳች መኖሪያ እንድትሆን ነበር። የሰው ልጆች ሕይወት ከዕፅዋትም ሆነ ከእንስሳት ሕይወት የላቀ ዓላማ አለው። ምክንያቱም እኛ ፈጣሪያችን ማን እንደሆነ ማወቅ የምንችል ሲሆን የእሱን ፍቅርና ፍትሕ ልናደንቅ ብሎም በእነዚህ ባሕርያቱ ልንመስለው እንችላለን።—መክብብ 12:13ን እና ሚክያስ 6:8ን አንብብ።

ፈጣሪያችን ዓላማውን ሁሉ ከግብ ማድረስ ይችላል። በመሆኑም ወደፊት መከራንና የፍትሕ መጓደልን እንደሚያስወግድ እንዲሁም ምድርን ለሰው ዘር አስደሳች መኖሪያ እንደሚያደርጋት እርግጠኞች መሆን እንችላለን።—መዝሙር 37:11, 29፤ ኢሳይያስ 55:11ን አንብብ።