መዝሙር 139
በአዲሱ ዓለም ስትኖር ይታይህ
-
1. እኔም አንተም፣ ሁላችንም፣
ይታይህ ስንኖር ባዲስ ዓለም።
ነፃ መሆን፣ ሰላም ማግኘት
አቤት እንዴት እንደሚያስደስት!
ያምላክ መንግሥት እንከን የለው፤
ጨርሶ አይኖርም ክፉ ሰው።
ጊዜው ደርሷል ባዲስ ዓለም ለመኖር፤
ያብቃን ከልባችን
ላምላክ ለመዘመር፦
(አዝማች)
“አምላካችን ሆይ፣ እናመስግንህ፤
ሁሉን ነገር አዲስ በማድረግህ።
እንዘምር በደስታ እናቅርብ ምስጋና፣
ውዳሴና ክብር ’ሚገባህ ነህና።”
-
2. እኔም አንተም፣ ባዲስ ዓለም፣
ይታይህ ስንኖር ለዘላለም።
የምናየው፣ የምንሰማው
አያስፈራም፤ አያሰጋንም።
ይፈጸማል የአምላክ ቃል፤
ድንኳኑም ከኛ ጋር ይሆናል።
በሞት ያንቀላፉትንም ያስነሳል፤
እነሱም ከኛ
ጋር ያመሰግኑታል፦
(አዝማች)
“አምላካችን ሆይ፣ እናመስግንህ፤
ሁሉን ነገር አዲስ በማድረግህ።
እንዘምር በደስታ እናቅርብ ምስጋና፣
ውዳሴና ክብር ’ሚገባህ ነህና።”
(በተጨማሪም መዝ. 37:10, 11ን፣ ኢሳ. 65:17ን፣ ዮሐ. 5:28ን እና 2 ጴጥ. 3:13ን ተመልከት።)