መዝሙር 151
አምላክ ይጣራል
-
1. የሰው ሕይወት ጠፊ ነው እንፋሎት፤
ዛሬ ታይቶ ለቅጽበት።
ስንሞት ሁሉም ነገር ያከትማል፤
እንባ፣ ሐዘን ይነግሣል።
ሰው ይነሳል ወይ አንዴ ከሞተ?
አምላክ ቃል ገብቶልናል፦
(አዝማች)
ይጣራል፤ ይመልሳሉ፤
በሕይወት ይኖራሉ።
የ’ጁ ሥራዎች ናቸው፤
ይጓጓል ሊያስነሳቸው።
እንግዲያው እምነት ይኑርህ፤
ይሖዋ ’ንደሚያስነሳህ።
የ’ጁ ሥራ ስለሆ’ን
ዘላለም እ’ኖራለን።
-
2. ያምላካችን ወዳጆች ቢሞቱም
በፍጹም አይረሱም።
ያንቀላፉ፣ ባምላክ መዝገብ ያሉ፣
ቃል ገብቷል ይነቃሉ።
ከዚያም አንድ ላይ እንኖራለን
በገነት ለዘላለም።
(አዝማች)
ይጣራል፤ ይመልሳሉ፤
በሕይወት ይኖራሉ።
የ’ጁ ሥራዎች ናቸው፤
ይጓጓል ሊያስነሳቸው።
እንግዲያው እምነት ይኑርህ፤
ይሖዋ ’ንደሚያስነሳህ።
የ’ጁ ሥራ ስለሆ’ን
ዘላለም እ’ኖራለን።
(በተጨማሪም ዮሐ. 6:40፤ 11:11, 43ን እና ያዕ. 4:14ን ተመልከት።)