በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ

ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ

አውርድ፦

  1. 1. ከንቅልፌ ነቃሁ ማለዳ፤

    በወፎች ጣፋጭ ዜማ።

    ደስ የሚል፣ ብሩህ ቀን መጣ፤

    ፀሐይ ፍንትው ብላ ስትወጣ።

    እንዲህ ነው ሕይወት ያኔ፤

    ሰላም፣ ጤና ነው ሁሌ።

    ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ፤

    ሌሊቱ ሊነጋ ነው።

  2. 2. ማልጄ ወጣሁ ከደጄ፤

    መስኩን ላይ አሻግሬ።

    ሙዚቃ ነው ለጆሮዬ፤

    ጅረቱ ሲፈስ በዝማሬ።

    ማዶ ይታያል ማሳው፣

    እህል ሸፍኖት ጋራው።

    ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ፤

    ሌሊቱ ሊነጋ ነው።

    (መሸጋገሪያ)

    ናፍቄያለሁ፣ ጓጉቻለሁ፤

    ያኔ መኖር እመኛለሁ፤

    ታሪክ ሲሆን እንባ፣ ለቅሶ

    ሕልሜ ሁሉ እውን ሆኖ።

  3. 3. ደስታ፣ ሐሴት ነው ዙሪያዬ

    ባምላክ ሕዝብ ተከብቤ።

    ጀምበር እስክትገባ ማታ

    መዝሙር ይሰማል ሁሉ ቦታ።

    አውርተን አንጠግብም ገና

    የይሖዋን ውለታ።

    ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ፤

    ሌሊቱ ሊነጋ ነው።

    (መሸጋገሪያ)

    ይታየኛል አቤት ያኔ!

    የናፈቁኝን አግኝቼ፣

    በደስታ ’ንባ ስንላቀስ፣

    የልባችን ምኞት ሲደርስ።

  4. 4. ያብቃኝ ለዚያ ጊዜ፣

    ለምጓጓለት ዘመን።

    አምላክ ነው ተስፋ የሰጠው፤

    አይዋሽም፣ ለቃሉ ታማኝ ነው።

    ገና ባሳብ እረካለሁ

    ሳሰላስል በተስፋው።

    ሩቅ አይደለም አውቃለሁ፤

    ሌሊቱ ሊነጋ ነው።