በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተ ግራ፦ ወንድም ዬቭጌኒ ስቴፋኒዲን። በስተ ቀኝ፦ ወንድም አሌክሳንደር ቮትያኮቭ

ሚያዝያ 23, 2024 | የታደሰው፦ ጥቅምት 25, 2024
ሩሲያ

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ተፈረደባቸው | ይሖዋን ማገልገል ትልቅ መብት ነው

ወቅታዊ መረጃ—ወንድሞች ተፈረደባቸው | ይሖዋን ማገልገል ትልቅ መብት ነው

ጥቅምት 25, 2024 በኡድሙርቲያን ሪፑብሊክ፣ በኢዢፍስክ ከተማ የሚገኘው የፐርቮማይስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ዬቭጌኒ ስቴፋኒዲን እና ወንድም አሌክሳንደር ቮትያኮቭ ጥፋተኛ ናቸው የሚል ብይን አስተላልፏል። ዬቭጌኒ የስድስት ዓመት፣ አሌክሳንደር ደግሞ የስድስት ዓመት ከስድስት ወር የገደብ እስራት ተፈርዶባቸዋል። አሁን ወህኒ አይወርዱም።

አጭር መግለጫ

እንደ አሌክሳንደር እና ዬቭጌኒ ሁሉ እኛም በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ለይሖዋ ‘ያለፍርሃት ቅዱስ አገልግሎት ማቅረብ’ መቻል ትልቅ መብት እንደሆነ ይሰማናል።​—ሉቃስ 1:74, 75

የክሱ ሂደት

  1. ሚያዝያ 14, 2021

    የደህንነት ሰዎች የዬቭጌኒን ቤት ፈተሹ

  2. ታኅሣሥ 13, 2022

    አሌክሳንደር እና ዬቭጌኒ የወንጀል ክስ ተመሠረተባቸው

  3. ታኅሣሥ 14, 2022

    ፖሊሶች የሁለቱንም ቤቶች ፈተሹ። አሌክሳንደር ጣቢያ እንዲያድር ተደረገ። ዬቭጌኒ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  4. ታኅሣሥ 15, 2022

    አሌክሳንደር ከጣቢያ ተለቀቀ፤ የቁም እስረኛ ተደረገ

  5. ሰኔ 9, 2023

    አሌክሳንደር ከቁም እስር ተፈታ፤ የጉዞ ገደቦች ተጣሉበት

  6. ነሐሴ 17, 2023

    ክሳቸው በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ