ጥቅምት 18, 2024
ሩሲያ
‘ይሖዋ ይክሰኛል’
በክራስኖዳር ግዛት የሚገኘው ቭይሴልኮቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ከእህት ቫሲሊና ፕዬንስካያ ጉዳይ ጋር በተያያዘ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል። አቃቤ ሕጉ እንዲተላለፍባት የሚፈልገውን ብይን ገና አላሳወቀም።
አጭር መግለጫ
ይሖዋ፣ ስደትን እየተጋፈጠ ያለ እያንዳንዱን አገልጋዩን እንደሚመለከተውና ‘ሥራው ወሮታ እንዳለው’ እንደሚያረጋግጥለት በማወቃችን አመስጋኞች ነን።—ኤርምያስ 31:16
የክሱ ሂደት
የካቲት 13, 2022
ቤቷ ተፈተሸ
ግንቦት 23, 2023
የክስ ፋይል ተከፈተባት። የተወነጀለችው ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ከሌሎች ጋር በመወያየቷና የይሖዋ ምሥክሮች በሚያደርጓቸው ሰላማዊ ሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፏ ነው። የባንክ ሒሳቧ ታገደ።
ሐምሌ 18, 2023
የጉዞ ገደብ ተጣለባት
ጥር 31, 2024
ክሷ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ