በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 13, 2021
ቱርክሜኒስታን

የቱርክሜኒስታን ወታደራዊ ፍርድ ቤት በወንድም ሩስላን አርትየክማየራዶቭ ላይ የሁለት ዓመት እስራት ፈረደበት

የቱርክሜኒስታን ወታደራዊ ፍርድ ቤት በወንድም ሩስላን አርትየክማየራዶቭ ላይ የሁለት ዓመት እስራት ፈረደበት

ጥር 11, 2021 የቱርክሜኒስታን ወታደራዊ ፍርድ ቤት ወንድም ሩስላን አርትየክማየራዶቭ ጥፋተኛ ነው የሚል ውሳኔ ያሳለፈ ሲሆን የሁለት ዓመት እስር በይኖበታል። ወንድም ሩስላን በገለልተኛ አቋሙ ምክንያት ሲታሰር ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው።

ወንድም ሩስላን ውሳኔውን ከሰማ በኋላም መንፈሱ አልተደቆሰም፤ ደስታውም አልጠፋም። ወደ እስር ቤት ሲወሰድ ኢየሱስ በማቴዎስ 24:13 ላይ ‘እስከ መጨረሻው የጸና ይድናል’ በማለት የተናገረውን ሐሳብ ጠቅሷል።

በቱርክሜኒስታን ያሉ ወጣት ወንድሞች የሚያሳዩት እምነት እኛንም ያበረታታናል። “ከፊቱ ለሚጠብቀው ደስታ ሲል” እስከ መጨረሻ የጸናውን የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ፈቃደኞች ናቸው።—ዕብራውያን 12:2