በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የወጣቶች ጥያቄ

የጽሑፍ መልእክት ስለ መለዋወጥ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?

የጽሑፍ መልእክት ስለ መለዋወጥ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?
  • ) የጽሑፍ መልእክትን በጥበብ ከተጠቀምክበት ከሰዎች ጋር ለመገናኘት ጥሩ መንገድ ነው።

  • ( አላግባብ ከተጠቀምክበት ግን ከሌሎች ጋር ያለህን ግንኙነትና መልካም ስምህን ሊያበላሽብህ ይችላል።

ይህ ርዕስ ከጽሑፍ መልእክት ጋር በተያያዘ ስለሚከተሉት ጉዳዮች እንድታውቅ ይረዳሃል፦

በተጨማሪም በዚህ ርዕስ ውስጥ የሚገኙ፦

 የምትልከው ለማን ነው?

 በርካታ ወጣቶች፣ የጽሑፍ መልእክት ከሌሎች ጋር ለመገናኘት የሚያስችል በጣም አስፈላጊ ዘዴ እንደሆነ ይሰማቸዋል። የጽሑፍ መልእክት በመለዋወጥ ከፈለግኸው ሰው ጋር መገናኘት ትችላለህ፤ እርግጥ ነው፣ ይህን ማድረግ የምትችለው ወላጆችህ ከፈቀዱልህ ነው።

 “እኔና እህቴ ከወንዶች ጋር ስናወራ አባቴ ደስ አይለውም። ማውራት ቢኖርብን እንኳ ይህን ማድረግ የምንችለው በቤት ስልክ ያውም ሳሎን ውስጥ ሰው ባለበት ነው።”​—ለኖር

 ልታውቀው የሚገባ ነገር፦ የስልክ ቁጥርህን ለማንኛውም ሰው የምትሰጥ ከሆነ ችግር ሊያጋጥምህ ይችላል።

 “የስልክ ቁጥርህን ማንንም ሳትመርጥ ለሁሉም ሰው የምትሰጥ ከሆነ የማትፈልጋቸው መልእክቶች ወይም ምስሎች ሊደርሱህ ይችላሉ።”​—ስኮት

 “ተቃራኒ ፆታ ካለው ሰው ጋር ሁልጊዜ የጽሑፍ መልእክት የምትለዋወጥ ከሆነ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፍቅር ሊይዝህ ይችላል።”​—ስቲቨን

 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል።” (ምሳሌ 22:3) አንዳንድ ጥንቃቄዎችን በማድረግ ራስህን ከብዙ ችግር መጠበቅ ትችላለህ።

 እውነተኛ ታሪክ፦ “ጓደኛዬ ከሆነ አንድ ልጅ ጋር ሁልጊዜ የጽሑፍ መልእክት እንላላክ ነበር። ከዚህ ልጅ ጋር ከጓደኝነት ያለፈ ግንኙነት እንደሌለን አስብ ስለነበር ይህን ማድረጋችን ችግር ያለው አልመሰለኝም። በኋላ ግን ልጁ እንደወደደኝ ነገረኝ። አሁን መለስ ብዬ ሳስበው ከልጁ ጋር ይህን ያህል መቀራረብ እንዲሁም ሁልጊዜ የጽሑፍ መልእክት መለዋወጥ አልነበረብኝም።”​—ሜሊንዳ

 እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ሜሊንዳ፣ ጓደኛዋ ስሜቱን ከነገራት በኋላ ከእሱ ጋር የሚኖራት ግንኙነት ምን የሚሆን ይመስልሃል?

 ታሪኩን በሌላ መልክ ለማሰብ ሞክር! ሜሊንዳ ከዚህ ልጅ ጋር ያላት ግንኙነት ከጓደኝነት እንዳያልፍ ምን ማድረግ ትችል ነበር?

 የምትልከው ምንድን ነው?

 የጽሑፍ መልእክቶችን መለዋወጥ ቀላል እና አስደሳች በመሆኑ የጻፍኸው ነገር ለተቀባዩ የተሳሳተ መልእክት ሊያስተላልፍ እንደሚችል ልብ ላትል ትችላለህ።

 ልታውቀው የሚገባ ነገር፦ ሰዎች፣ በጽሑፍ የምትልከውን መልእክት ባላሰብኸው መንገድ ሊረዱት ይችላሉ።

 “የጽሑፍ መልእክት ስትለዋወጥ ግለሰቡ ስሜቱ ምን እንደሆነ ማወቅ ወይም የድምፁን ቃና መስማት አትችልም፤ ስሜትን ለመግለጽ የሚያስችሉ ምልክቶችን መልእክታችን ውስጥ ብናካትትም እንኳ በዚህ ረገድ ያን ያህል አይረዱንም። በመሆኑም መልእክትህ ያላሰብኸውን ሐሳብ ሊያስተላልፍ ይችላል።”​—ብሪያና

 “አንዳንድ የማውቃቸው ሴቶች፣ ለወንዶች በጻፏቸው መልእክቶች የተነሳ እንደሚያሽኮረምሙ የተወራባቸው ከመሆኑም ሌላ ስማቸው ጠፍቷል።”​—ሎራ

 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ደጋግ ሰዎች ከመናገራቸው በፊት ያስባሉ።” (ምሳሌ 15:28 የ1980 ትርጉም) ከዚህ ጥቅስ ምን እንማራለን? የጻፍኸውን መልእክት ከመላክህ በፊት ደግመህ አንብበው።

 የምትልከው መቼ ነው?

 የማመዛዘን ችሎታህን በመጠቀም፣ ከጽሑፍ መልእክት ጋር በተያያዘ የምትከተላቸውን የራስህን ደንቦች ማውጣት ትችላለህ።

 ልታውቀው የሚገባ ነገር፦ የጽሑፍ መልእክት ከመለዋወጥ ጋር በተያያዘ ጥሩ ምግባር የማታሳይ ከሆነ ሰዎች ሥርዓት እንደሌለህ እንዲሰማቸው ልታደርግ ትችላለህ፤ ይህ ደግሞ ጓደኞችህ እንዲርቁህ ሊያደርግ ይችላል።

 “ከጽሑፍ መልእክት ጋር በተያያዘ ሳታስበው ጥሩ ያልሆነ ምግባር ልታሳይ ትችላለህ። ከሌላ ሰው ጋር እየተጨዋወትሁ ወይም ምግብ እየበላሁ ሳለም እንኳ ሳላስበው የጽሑፍ መልእክት የምልክበት ጊዜ አለ።”​—አሊሰን

 “መኪና እየነዱ የጽሑፍ መልእክት መለዋወጥ አደገኛ ነው። መኪና ስትነዳ ትኩረትህ መንገዱ ላይ ካልሆነ አደጋ ሊደርስብህ ይችላል።”​—አን

 መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው፤ . . . ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው።” (መክብብ 3:1, 7) ይህ ሐሳብ ከማውራት ጋር ብቻ ሳይሆን የጽሑፍ መልእክት ከመለዋወጥ ጋር በተያያዘም ይሠራል!

 ጠቃሚ ምክር

የምትልከው ለማን ነው?

  •  ;-)ወላጆችህ የሚሰጡህን መመሪያ ታዘዝ።​—ቆላስይስ 3:20

  •  ;-)የስልክ ቁጥርህን ላገኘኸው ሰው ሁሉ አትስጥ። እንደ ስልክ ቁጥር ያሉ የግል መረጃዎችህን ለሚጠይቁህ አንዳንድ ሰዎች ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆንህን አክብሮት በተሞላበት መንገድ መግለጽን ተማር፤ ይህን መማርህ አዋቂ ስትሆንም ይጠቅምሃል።

  •  ;-)ሌላኛው ወገን የፍቅር ስሜት እንዲፈጠርበት የሚያደርጉ የጽሑፍ መልእክቶችን አትላክ። የፍቅር ግንኙነት ለመመሥረት ሳታስብ እንዲህ ማድረግ ለብስጭት እና ለሐዘን ይዳርጋል።

 “በሞባይል ስልክ አጠቃቀሜ ረገድ ወላጆቼ እንዲተማመኑብኝ አድርጌያለሁ፤ በመሆኑም ወላጆቼ በሞባይል ስልክ ከማገኛቸው ሰዎች ጋር በተያያዘ ስጋት አያድርባቸውም።”​—ብሪያና

የምትልከው ምንድን ነው?

  •  ;-)አንድ መልእክት ከመጻፍህ በፊት ራስህን እንዲህ እያልህ ጠይቅ፦ ‘ግለሰቡን ለማነጋገር የተሻለው አማራጭ የጽሑፍ መልእክት ነው?’ አንዳንድ ጊዜ ስልክ መደወል ወይም ከግለሰቡ ጋር በአካል ተገናኝቶ ማውራት የተሻለ ሊሆን ይችላል።

  •  ;-)ለግለሰቡ ፊት ለፊት ለመናገር የማትደፍረውን ነገር በጽሑፍ አትላክ። የ23 ዓመቷ ሣራ “አፍ አውጥታችሁ ለመናገር የሚከብዳችሁ ነገር ከሆነ በጽሑፍ ልትልኩት አይገባም” ብላለች።

 “አንድ ሰው የፆታ ስሜት የሚቀሰቅሱ ምስሎችን ቢልክላችሁ ጉዳዩን ለወላጆቻችሁ ንገሯቸው። እንዲህ ማድረጋችሁ ጥበቃ የሚሆንላችሁ ከመሆኑም ሌላ ወላጆቻችሁ በእናንተ ላይ እምነት እንዲጥሉ ያደርጋል።”​—ሲርቫን

የምትልከው መቼ ነው?

  •  ;-)የሞባይል ስልክ የማትጠቀምባቸውን ወቅቶች አስቀድመህ ወስን። ኦሊቪያ የተባለች ወጣት እንዲህ ብላለች፦ “በምግብ ሰዓት ወይም በማጠናበት ወቅት ስልኬን አልይዘውም። በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ በምሆንበት ጊዜ ደግሞ ስልኬን አውጥቼ ለመመልከት እንዳልፈተን ስል አጠፋዋለሁ።”

  •  ;-)የሌሎችን ስሜት ከግምት አስገባ። (ፊልጵስዩስ 2:4) ከሌሎች ጋር እያወራህ የጽሑፍ መልእክት አትለዋወጥ።

 “ለራሴ ደንቦችን አውጥቻለሁ፤ ለምሳሌ ያህል፣ የግድ ካልሆነ በስተቀር ከጓደኞቼ ጋር በምሆንበት ጊዜ ከሌሎች ጋር የጽሑፍ መልእክት አልለዋወጥም። እንዲሁም ለማልቀርባቸው ሰዎች የስልክ ቁጥሬን አልሰጥም።”​—ያኔሊ